የንጋቱ ኮከብ
Yenegatu Kokeb
2009 · ትራክ 3 · 5:08 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
(አዝማች)
የንጋቱ ኮከብ ውበቱ ያማረ፣
ከምንም ከማንም በላይ የከበረ፣
እሱ ነው ጌታዬ፥እኔ የማመልከው
ምሕረቱን አብዝቶ ልቤን ያሳረፈው
ቁጥር 1 · Verse 1
(ቁ 1)
ብዙ ክብር ያርግ ወደ ማደሪያው፣
ዙፋኑን ይክበበው ስለሚገባው፤
አለ የተባለ አዳኝ ብቸኛ መድኃኒት፣
ኢየሱስ እሱ ነው አሁንም ወደፊት
የንጋቱ ኮከብ ...
ቁጥር 2 · Verse 2
(ቁ 2)
ዳግመኛ ተወለድሁ ክፉ ደጉን ለየሁ ፣
አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ አሮጌውን ሻረው
የታረደውን በግ አለቃዬ ኢየሱስ፣
ሾምኩት በሕይወቴ ላይ ሊገዛ እንደ ንጉሥ
የንጋቱ ከክብ...
ቁጥር 3 · Verse 3
(ቁ 3)
እንዲሁ ወደደኝ ከነምናምኔ፣
ትቼ ተከተልኩት፣ ይቺ ዓለም ለምኔ?
ማንም ያልሰጠኝን ሰላምና ደስታ
አግኝቻለሁ ከላይ ከሠራዊት ጌታ
የንጋቱ ኮከብ..
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ