ይብዛልህ እንጂ ምስጋና
Yibzalih Enji Misgana
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ይብዛልህ እንጂ ምስጋና
ይብዛልህ እንጂ አምልኮዬ
ይብዛልህ እንጂ ክብር
ይብዛልህ እንጂ ጌታዬ
ማብዛት ለኔ ጥማቴ ነው
ያለኝ የምሰጠው ይህን ነው
በዘመኔ ሁሉ የማልመልሰው ውለታ አለብኝ
የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ለኔ ያደረገልኝ
ብዘረዝረው ደግሞም ባወራው ከቁጥር ሁሉ በዛ
እኔም በአለኝ ሀይሌ ምስጋና ለእሱ ላብዛ
አዝማች · Chorus
ይብዛልህ እንጂ ምስጋና...
ቁጥር 2 · Verse 2
አቤቱ አምላኬ ሆይ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ
ክብርና ግርማ ብርሃንን እንደ ልብስ ለብሰህ
በላይ በሰማይ ተውበህ በዙፋንህ ተቀምጠህ
በፈጠርካቸው ፍጥረታት ሁሌ ትወደሳለህ
አዝማች · Chorus
ይብዛልህ እንጂ ምስጋና...
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር በሰማይ የሚስተካከለው ማነው
በዙሪያው ካሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው
ስለዚህ በምስጋና ከፍ በል በእልልታ
እጥፍ ድርብ ይሁንልህ ተመስገንልን ጌታ
አዝማች · Chorus
ይብዛልህ እንጂ ምስጋና...
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ