Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይወደናል

Yiwedenal

ትራክ 5 · 5:53 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አለም ሳይፈጠር ሳንወለድ ያውቀናል

ሃጥያተኞች ሳለን እንዲሁ ወዶናል

ሳንወድው ወዶናል/4

በቃ አለም ብጠላን

በቃ የሱስ ወዶናል

በቃ ማንም ቢከሰን

በቃ ወዶ አፅድቆናል

ይወደናል ይወደናል ጌታ እየሱስ ይወደናል/2

እህህ ወረት በሌለበት በዘላለም ፍቅር

እህህ መች ወዳጅ ተወዶ እንኳን ጠላት ይቅር

አሄሄ የለምንም ምክኒያት እየሱስ ወደደን

አሄሄ ሞታችንን ወስዶ የሱን ህይወት ሰጠን

ይወደናል ይወደናል ጌታ እየሱስ ይወደናል/2

እህህ እየሱስ መስቀል ላይ አንገቱን በደፋ

እህህ ከጨለማ ወጣን ሆነን ብርሃን ተስፋ

አሄሄ የአለም ሽንገላ ፍቅሁ አይታየንም

አሄሄ ከሞተልን በላይ ማንም አይወደንም

በቃ አለም ብጠላን

በቃ የሱስ ወዶናል

በቃ ማንም ቢከሰን

በቃ ወዶ አፅድቆናል

ይወደናል ይወደናል ጌታ እየሱስ ይወደናል/2

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ