አገልጋይ
Agelgay
2013 · ትራክ 1 · 6:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የአምላክን ድምፅ ሰሚ መልካሙን አላሚ
በትጋት አገልጋይ ብድራቱን የሚያይ
አገልጋይ
መቼ ቆረቆረው የምድር ላይ ትግሉ
አምላኩን የሚወድ የሚኖር በቃሉ
አገልጋይ
ድንገት ተፈትኖ ቢቀል በሚዛኑ
የሚገፋው በዛ ጠፋ ገላጋዩ
እግዚአብሔር ተፋው ብለው ተናገሩ
በብርታቱ ጊዜ አለህ ወይ ያላሉ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔ ነኛ ያ ሰው ማረኝ በመስቀል የሞትክልኝ
በፍቅር የፈለኩህን አትርሳው የትላንቱን
በፍቅር የፈለኩህን አትርሳው የትላንቱን (፪x)
በቅንነት ያገለገልኩህ
ሥምህን በመጥራት የተከተልኩህ
ሊደክም ነው ዛሬ ጉልበቴ ጉልበቴ
አስበኝ አስበኝ ኢየሱስ አባቴ (፪x)
እኔ ነኛ ያ ሰው ማረኝ በመስቀል የሞትክልኝ
በፍቅር የፈለኩህን አትርሳው የትላንቱን
በፍቅር የፈለኩህን አትርሳው የትላንቱን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የአምላክ ድምፅ ሰሚ መልካሙን አላሚ
በትጋት አገልጋይ ብድራቱን የሚያይ
አገልጋይ
መቼ ቆረቆረው የምድር ላይ ትግሉ
አምላኩን የሚወድ የሚኖር በቃሉ
አገልጋይ
ድንገት ተፈትኖ ቢቀርብ በሚዛኑ
የሚገፋው በዛ ጠፋ ገላጋዩ
እግዚአብሔር ጠፋው ብለው ተናገሩ
በብርታቱ ጊዜ አለህ ወይ ያላሉ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ነኛ ሰው ማረኝ (ማረኝ)
በመስቀል የሞትክልኝ (የሞትክልኝ)
በፍቅር የፈለኩህን አትርሳው የትላንቱን (አትርሳው የትላንቱን)
በፍቅር የፈለኩህን አትርሳው የትላንቱን (፪x)
አትርሳው የትላንቱን (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ በሰራኸው እራሱን ሲያሳይ
የአንተን መንገድ ትቶ በራሱ ሲዋኝ
ስለራሱ ሲያውጅ ጉራውን ሲነዛ
ስንቱ መና ቀረ ስንቱ ሆነ ጤዛ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔ ነኛ ሰው ማረኝ (ማረኝ)
በመስቀል የሞትክልኝ (የሞትክልኝ)
በፍቅር የፈለኩህን አትርሳው የትላንቱን (አትርሳው የትላንቱን)
በፍቅር የፈለኩህን አትርሳው የትላንቱን (፪x)
አትርሳው የትላንቱን (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ