በቃ
Beqa
2013 · ትራክ 3 · 7:11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በቃ የሰቆቃው ኑሮ
ለየለት ደረሰ ዘንድሮ
በሰላም ሂድ አለኝ
ሕይወቴን ቀይሮ
ቁጥር 1 · Verse 1
በቃ የሰቆቃው ኑሮ
ለየለት ደረሰ ዘንድሮ
በሰላም ሂድ አለኝ
ሕይወቴን ቀይሮ (፪x)
ሰላሳ ስምንት አመት
በአልጋዬ ላይ እኔ ተኝቼ (ኦሆ ኦሆ)
መልዓኩ ሲያናውጠው
ወደ ውሃው ሚከተኝ አጥቼ (ኦሆ ኦሆ)
አቅም የለኝ ወገን የለኝ
ውስጤ እያለ ተማረረ (ኦሆ ኦሆ)
እምባ ቀደሙት ዓይኖቼ
ልቤም እጅጉን አዘነ
አበቃልኝ በቃ ዛሬ
ሊቀጥል ነው የእኔ ህመሜ
ብዬ ሳስብ በትካዜ
ጌታ ቆሟል ከአጠገቤ (፪x)
አዝማች · Chorus
በቃ የሰቆቃው ኑሮ
ለየለት ደረሰ ዘንድሮ
በሰላም ሂድ አለኝ
ሕይወቴን ቀይሮ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጨለማ ነው የእኔ ኑሮ
ብርሃን አጥቶ ዓይኔ ታውሮ (ኦሆ ኦሆ)
ወጣሁ ምጽዋትን ጥየቃ
እንደድሮ እንደወትሮ (ኦሆ ኦሆ)
ምንድነው ኢሄ ጩኸቱ
ብዬ ጠየኩ የሚያልፍ ሰው (ኦሆ ኦሆ)
ኢየሱስ በዚህ መጥቶ ነው
ፈዋሹ እያለፈ ነው
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ
አላለፍከኝ አባብዬ
ፊትህንም አዞርክልኝ
ጨለማዬን ገፈፍክልኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
በቃ የሰቆቃው ኑሮ
ለየለት ደረሰ ዘንድሮ
በሰላም ሂድ አለኝ
ሕይወቴን ቀይሮ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምንድነው እርሱ በዛብኝ
ችግርና መከራዬ (ኦሆ ኦሆ)
የሞት ጥላ አጠላብኝ
አታየኝም ወይ ጌታዬ (ኦሆ ኦሆ)
ከአባቶቼ እንደተማርኩት
ከቃልህ እንዳነበብኩት (ኦሆ ኦሆ)
ጩኸት ሰምተህ መልሰሃል
ለስንቱ ሕይወት ሆነሃል
የእኔስ ቀን መቼ ነው አልኩኝ
ተንበርክኬ ተማጸንኩኝ
ጸሎቴም ተሰማልኝ
የእኔ ጌታ በቃህ አለኝ (፪x)
በቃ በቃ በቃ
በቃ በቃ በቃ
የሰቆቃው ዘመን
ከእኔ ላይ አበቃ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ