አምልኮዬ
Amelkoyie
ትራክ 6 · 6:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምልኮዬ ይገባሃል
ላምልከው እያልኩኝ እወደዋለሁኝ
የመስቀሉን ሚስጥር ፍቅር እያየሁኝ፥
ውለታው ስለ እኔ እጅግ በዝቷልና
እኔም አበዛለው ለስሙ ምስጋና
የተነሱበትን ጥሎ አዋረዳቸው
ስልጣኑን ቀምቶ ባዶ አደረጋቸው
እነማን በርትተው እግዚአብሔርን ሻሩ
እርሱ እኮ ይኖራል በነበረ ክብሩ
አዝማች · Chorus
ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(4)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅጄ አመልከዋለው ወድጄ እንብረከካለው
ልናገር ከምችለው በላይ ትልቅ ነው የክንዱ ስልጣን
ገብቶኛል እዘምራለው ስልጣኑ ከማንም በላይ ነው
እንዴት ልናወጥ እንዴትስ ልፍራ
እያየው እክንዱን ስራ
ተደላድዬ ቆሚያለው
ሃያሉን ክንዱን ይዣለው
ሊሰራ እርሱ ሲነሳ
እያየው ሁሉም ይታዘዛል
አዝማች · Chorus
ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(4)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሃያል ነን ጎበዝ ነን ያሉ
በእርሱ ላይ ብዙ ፎከሩ
ታገሰ ዘመን ሰጣቸው
ታበዪ ክንዱ አጠፋቸው
በዘመን በታሪክ የለም
ስልጣኑ ፍጹም አልተሻረም
ቁጥር 4 · Verse 4
ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(8)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ