ኢየሱስ ለእኔም ጌታ ነው
Eyesus Leniem Gieta New
ትራክ 5 · 5:19 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር ሆይ አመሰግናለሁ
ልጅህን ባትሰጠኝ ኖሮ እንዴት እሆናለሁ?
ፈቅደህ ስትልከው ወደዚህ ምድር
አስበህ አይደለም ወይ እኔ እንድድን
እግዚአብሔር ሆይ ፍቅርህ ይገርመኛል
ከስጦታ በላይ ልጅህን ሰጥተኸናል፥
ጊዜው ሰሆነ የመከፈቻው
በር ተከፈተ ቃል ስላዘዘው
ያሳፈረኝ ችግር ሲርቅ
ለምጼ ሁሉ ከእኔ ሲለቅ
ከሰው እኩል እኔም ስሆን
ዝም ማለት አቅቶኛል
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ለእኔም ደርሶልኛል
ኢየሱስ
ለእኔም ጌታ ነህ(3)
ምን እልሃለው?
ለሰራኸው ስራ ክብር እሰጥሃለው
ክብሬን ጥዬልህ ፊት እሰግዳለው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሀጥያት (?) የጠፈረኝ
ሽባ አድርጎ ያስቀመጠኝ
ዛሬስ ጌታ አስቦኛል
ድንቅ አምላክ ነው ፈውሶኛል
ንጹህ ነሽ ብሎ አቁሞኛል
አዝማች · Chorus
ጊዜው ሰሆነ የመከፈቻው
በር ተከፈተ ቃል ስላዘዘው
እግዚአብሔር ሆይ ፍቅርህ ይገርመኛል
ከስጦታ በላይ ልጅህን ሰጥተኸናል
ቁጥር 3 · Verse 3
ስኖር ሳለው በጨለማ እየለመንኩ በከተማው
ማረኝ ብዬ ስማጸነው
ምሕረቱ መቼ ያልቅና
አኔም አየሁ እንደሌላ
ኢየሱስ
ለእኔም ጌታ ነህ(3)
ምን እልሃለው?
ለሰራኸው ስራ ክብር እሰጥሃለው
ክብሬን ጥዬልህ ፊት እሰግዳለው
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ሆይ አመሰግናለሁ
ልጅህን ባትሰጠኝ ኖሮ እንዴት እሆናለሁ?
ፈቅደህ ስትልከው ወደዚህ ምድር
አስበህ አይደለም ወይ እኔ እንድድን
እግዚአብሔር ሆይ ፍቅርህ ይገርመኛል
ከስጦታ በላይ ልጅህን ሰጥተኸናል፥
ጊዜው ሰሆነ የመከፈቻው
በር ተከፈተ ቃል ስላዘዘው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ