ብዙ ትቶልኛል
Bezu Tetolegnal
ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ብዙ ትቶልኛል ብዙ እወደዋለሁ
ብዙ እኔን ምሮኛል ብዙ አከብረዋለሁ
በብዙ ምሥጋና ፊቱ እቀርባለሁ
በብዙ ዝማሬ ጌታን አከብራለሁ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገበናን ሰው መግለጥ ይወዳል
ኃጢአትን መቼ ይቅር ይላል
የእኔ ውድ ከዝህ ሁሉ ልዩ (፪×)
ችሎኛል ሰዎች ይህንን ስሙኙ (፪×)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስንቆም ሞገስ የሚያለብሰን
ጻድቃኖች አድርጐ የቆጠረን
ኢየሱስ ብዙ ትቶልናል (፪×)
ምሕረት ዛሬም ያኖረናል (፪×)
ቁጥር 3 · Verse 3
ለመውገር ሁሉም ይቸኩላል
ድንጋዩን በእጁ ተሸሟል
ኢየሱስ የሰውን ድካም ያውቃል (፪×)
ከአመድ ላይ ምስኪኑን ያነሳል (፪×)
ቁጥር 4 · Verse 4
ውለታው ለእኔ በዝቶብኛል
ነውሬን ኢየሱስ ወስዶልኛል
ውበቴ ድምቀቴ ሽቶዬ (፪×)
ጠረኔ ሆነልኝ ጌታዬ (፪×)
አዝማች · Chorus
ብዙ ትቶልኛል ብዙ እወደዋለሁ
ብዙ እኔን ምሮኛል ብዙ አከብረዋለሁ
በብዙ ምሥጋና ፊቱ እቀርባለሁ (፬×)
በብዙ ዝማሬ ጌታን አከብራለሁ (፬×)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ