አንተ ግን ያው አንተ ነህ
Ante Gen Yaw Ante Neh
2013 · 6:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እስከዛሬ እኔ ያየሁት ሃ የተረዳሁት
መልካምነትህን ነዉ የማዉቀው አታውቅም ክፋት
ባለፍኩበት ሁሉ ከኔ ጋር የሆንክ
የልጅነቴ አምላክ እግዚአብሔር
አዝማች · Chorus
አይኔ ያየው ይሄንን ነው መልካምነትህን ነው
አይኔ ያየው ይሄንን ነው መልካምነትህን
አሃ መንገዴን ሁሉ እየመራኸኝ
ያልተለወጥክብኝ አንተ ብቻ ነህ
አንተ ግን አንተ ነህ አንተ ብቻ ነህ
ሁሉ ሲለዋወጥ አንተ ግን አንተ ነህ ኣትለዋወጥም
ነገር ሲለዋወጥ አንተ ግን አንተ ነህ አትለዋወጥም
በማደርያው ላይ ያለኸው በዙፋኑ ላይ ያለኸው አንተ ግን አንተ ነህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አንዴ ስንወድቅ አንዴ ስንነሳ
ያሳለፍነው ነገር እስኪ እንዴት ይወሳ
በጠራነው ጊዜ ለአፍታም ሳይዘገይ
እዚ ያደረሰን እሱ አይደለም ወይ
በማደርያው ላይ ያለው በዙፋኑ ላይ ያለው እሱ እንዴት ድንቅ ነው(፪x)
አዝማች · Chorus
ሁሉ ሲለዋወጥ አሃ አንተ ግን አንተ ነህ አትለዋወጥም
ነገር ሲለዋወጥ አሃ አንተ ግን አንተ ነህ አትለዋወጥም
በማደርያው ላይ ያለኸው በዙፋኑ ላይ ያለኸው አንተ ግን አንተ ነህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጭንቅ ጥብብ ብሎን ማን አለልኝ ስንል
በኛ ላይ ምክሩ በርትቶ ሲያይል
የተረሳን መስሎን ከመከራው ብዛት
ግን እሱ አቆመን እየሆነ አባት
በማደርያው: ላይ ያለኸው በዙፋኑ ላይ ያለኸው አንተ ግን አንተ ነህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሁሉ ሲለዋወጥ ኣሃ አንተ ግን አንተ አትለዋወጥም
ነገር ሲለዋወጥ ኣሃ አንተ ግን አንተ አትለዋወጥም
በማደርያው ላይ ያለው በዙፋኑ ላይ ያለው እርሱ እንዴት ድንቅ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከርሱ ጋር ስንጎዝ ባለፉት ዘመናት
ስንቴ አሳለፈን ክፉዎቹን ቀናት
እጃችንን ይዞ በድል እየመራ
እስከ ዛሬ ድረስ በምረቱ ኣቆመን
በማደርያው ላይ ያለው በዙፋኑ ላይ ያዉ እርሱ ድንቅ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ