ሞት መሻገሪያዬ
Mot Meshageriyayie
2013 · ትራክ 1 · 3:35 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሞት መሻገሪያዬ
ወደ ዘላለም ቤት ማለፊያዬ
የናፈቁትን የምወርስበት
አምላኬን የማገኝበት
የዘላለም ቤት መግቢያዬ
ሞት መሻገሪያዬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የእኔ ኑሮ በዚህ ምድር ላይ አያበቃም
ቆይታዬ መጨረሺያዬ በዚህ አይደለም
ይቀጥላል ከሞት ወዲያ በአዲስ ሕይወት
በዘለዓለም ቤት በደስታዬ ቤት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምኞቴን አይደለም የምናገረው
በእርግጥ የሚሆን የሚታይ ነው
በቃሉ እንደገባልኝ ቃል ኪዳን
ከሞት ወዲያ ከእርሱ ጋር እንደምሆን ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ሞትን ድል ነስቶልኛል
እንዴት ውጦ ያስቀረኛል
ተሻግሯል አልፏል ኑሮዬ
አልቀርም በሞት ተይዤ
ሞት ለእኔ ጥቅሜ ነው
ሞት ለእኔ ክብሬ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ