Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተ የእኔ

Ante Yenie

2012 · ትራክ 1 · 4:53 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አሃ! አሃሃ! (፪x)

በእጁ መዳፍ ላይ ቀርጾኛል

በሕይወት መዝገብ አስፍሮኛል

አንተ የእኔ ነህ ብሎኛል (፪x)

አዎ! እኔ የእርሱ

አዎ! እርሱም የእኔ

አዎ! የማገኘው

አዎ! ሁሌ ከጐኔ (፪x)

አሃ! አሃሃ! (፪x)

የከበረ ዋጋ ተከፍሎልኝ

በደሙ የተገኘሁ ልጁ ነኝ

አይደለም ጠላቴ እንደሚለው

መላው እኔነቴ የእርሱ ነው

የጌታ ነኝ ፣ የጌታ ነኝ

የኢየሱስ ነኝ ፣ የኢየሱስ ነኝ

ማንም አይችልም ፣ ማንም አይችልም

ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x)

ማንም አይችልም

ሊነጥለኝ

ዓላማው ፍቅር ነው

ለእኔ ያለው

ከሚያደርገው ነገር የማየው

እንደ ዓይኑ ብሌን የሚጠብቀኝ

ማን እንደርሱ ለእኔ ሊሆንልኝ

የጌታ ነኝ ፣ የጌታ ነኝ

የኢየሱስ ነኝ ፣ የኢየሱስ ነኝ

ማንም አይችልም ፣ ማንም አይችልም

ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x)

ማንም አይችልም

ሊነጥለኝ

በእጁ መዳፍ ላይ ቀርጾኛል

በሕይወት መዝገብ አስፍሮኛል

አንተ የእኔ ነህ ብሎኛል (፪x)

አዎ! እኔ የእርሱ

አዎ! እርሱም የእኔ

አዎ! የማገኘው

አዎ! ሁሌ ከጐኔ (፪x)

አሃ! አሃሃ! (፪x)

ውብና ድንቅ አድርጐ የፈጠረኝ

ለምሥጋናው ለአምልኮ ያጨኝ

የተፈጠርኩበት ውድ ዓላማ

ስለገባኝ ለእኔ

ሌላ አልሰማም

የጌታ ነኝ ፣ የጌታ ነኝ

የኢየሱስ ነኝ ፣ የኢየሱስ ነኝ

ማንም አይችልም ፣ ማንም አይችልም

ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x)

ማንም አይችልም

ሊነጥለኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ