ብቻውን ተዋግቶ የሚያሸንፍ
Bechawen Tewagto Yemiyashenef
2007 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ብቻውን ተዋግቶ የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
ታዲያ የምንፈራው ለምንድ ነው? (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የሰልፉ ባለቤት እግዚአብሔር
እንደ አህዛብ አማልክት ማይቀያየር
ባሪያዎቹን ከእሳት ውስጥ ያወጣል
በኃይሉ ከፍ ያለውን ያደርጋል (፪x)
አዝማች · Chorus
ብቻውን ተዋግቶ የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
ታዲያ የምንፈራው ለምንድ ነው? (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሰው ዓይን ሲታዩ አስፈሪዎች
በእግዚአብሔር ፊት ግን እጅግ ቀላለሎች
ጥላቸው ተገፏል ልባችን አይፍራ
ነገ ይሆኑልናል እንደ እንጀራ (፪x)
አዝማች · Chorus
ብቻውን ተዋግቶ የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
ታዲያ የምንፈራው ለምንድ ነው? (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ድል ለተነሳው ለጠላት ዛቻ
ለሚያስፈራራን በወሬ ብቻ
እጅ አንሰጥም ነገሩ ይገለበጣል
የእግዚአብሔር ሐሳብ ይፈጸማል (፪x)
አዝማች · Chorus
ብቻውን ተዋግቶ የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
ታዲያ የምንፈራው ለምንድ ነው? (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሁኔታዎችን አይቶ ተስፋ መቁረጥ
ወየሁ ጠፋሁ እያሉ መደናገጥ
አይሆንም ከእንግዲህ አባት አለን
በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን (፪x)
አዝማች · Chorus
ብቻውን ተዋግቶ የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
የእኛ ነው የሚያሸንፍ አምላክ
ታዲያ የምንፈራው ለምንድ ነው? (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ዘጸ. 15 3 ‹‹እግዚአብሔር ተወጊ ነው ስሙም… ›› [1]
ዘጸ. 14 14 ‹‹እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል …›› [2]
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ