በመጨረሻው ቀን
Bemechereshaw Qen
2007 · ትራክ 2 · 5:46 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ነገር ግን በመጨረሻው ቀን
ይመጣል የሚያስጨንቅ ዘመን [1]
የተባለው ጊዜው ይህ ነው
ይሻልሃል ወንድሜ ቆም ብለህ አስበው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ራሳቸውንና ገንዘብን የሚወዱ
ተድላን የሚፈልጉ እውነትን የሚክዱ
በቃኝን የማያውቁ የማያመሰግኑ
ይሆናሉ ተብሏል ሳያዩ የማያምኑ
ዘመኑ ክፉ ነው በጣም ያስፈራል
ኧረ ክርስቲያን ሆይ ብትነቃ ይሻላል (፪x)
አዝማች · Chorus
ነገር ግን በመጨረሻው ቀን
ይመጣል የሚያስጨንቅ ዘመን [1]
የተባለው ጊዜው ይህ ነው
ይሻልሃል ወንድሜ ቆም ብለህ አስበው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለጊዜያዊ ስልጣን ሌላውን የሚያሳድዱ
መልካምን የሚጠሉ ክፋትን የሚወዱ
ለወሬ የሚሮጡ ለሀሜት የሚቸኩሉ
የቀድሞውን ፍቅር ከውስጣቸው የጣሉ
በመንደርህ አሉ ለራስህ ጠንቀቅ በል
ዘመኑን ዋጅ እንጂ አጉል አጉል ቦታ አትዋል (፪x)
አዝማች · Chorus
ነገር ግን በመጨረሻው ቀን
ይመጣል የሚያስጨንቅ ዘመን [1]
የተባለው ጊዜው ይህ ነው
ይሻልሃል ወንድሜ ቆም ብለህ አስበው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍቅር የሌላቸው እርቅን የማይሰሙ
ለጥቅማቸው ሲሉ ፍትሕ የሚያጣምሙ
ምህረት የማያደርጉ ድሃን የሚበድሉ
እጅግ ብዙ ናቸው በአፍ የሚደልሉ
ያለ ሥርዓት ጥሰው የሚሄዱትን ሁሉ
ዝም አትበል ገስጽ ይህን ይላል ቃሉ (፪x)
አዝማች · Chorus
ነገር ግን በመጨረሻው ቀን
ይመጣል የሚያስጨንቅ ዘመን [1]
የተባለው ጊዜው ይህ ነው
ይሻልሃል ወንድሜ ቆም ብለህ አስበው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔ ከተመቸኝ ምን ቸገረኝ ባዮች
በቃሉ የማይኖሩ ሰነፍ ክርስቲያኖች
በዚህ ዓለም ንዋይ የሚደለሉ ሞኞች
ለሚያምኑ እንቅፋት የሚሆኑ ዝንጉዎች
አሉ በየአገሩ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ሽሽ
እልፍ በልና ይህን ዘመን ፈትሽ
ተላላ አትሁን ክርስቲያን ሆይ ንቃ
ከወጽመድ ልታመልጥ አንሳ የጦር ዕቃ
አዝማች · Chorus
ነገር ግን በመጨረሻው ቀን
ይመጣል የሚያስጨንቅ ዘመን [1]
የተባለው ጊዜው ይህ ነው
ይሻልሃል ወንድሜ ቆም ብለህ አስበው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ