በጎ ሰው
Bego Sew
2019 · ትራክ 2 · 4:50 · አማርኛ · ምስጋና
ቁጥር 1 · Verse 1
በጎ ሰው ከልቡ መዝገብ
በጎ ነገርን ያወጣል
የጌታን ቸርነት የቀመሰ
ለወንድሙ ይራራል
አዝማች · Chorus
እንዋደድ እንደ ቃሉ
እንተዛዘን በፍቅር
ዓለም እንዲያውቀን በዚህ
የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅር ታጋሽ ነው ቸርም ነው
አይቀናም አይታበይም
ሁሉን ያምናል ሁሉን ተስፋ ያደርጋል
ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም
አዝማች · Chorus
እንዋደድ እንደ ቃሉ
እንተዛዘን በፍቅር
ዓለም እንዲያውቀን በዚህ
የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት
ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ