Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የገና ብርሃን

Yegena Berhan

2019 · ትራክ 3 · 5:15 · አማርኛ · የገና

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በቤተልሔም ሌሊት ኮከብ በራ

ለእረኞች ተነገረ ታላቅ ዜና

አዳኝ ተወልዷል ዛሬ ለእናንተ

ክርስቶስ ጌታ በዳዊት ከተማ

ስብሐት ለእግዚአብሔር በአርያም

ሰላም በምድር ለሰው ልጆች

የገና ብርሃን ፈንጥቋል ዛሬ

እንሂድ እንስገድ ለተወለደው

ሰማይ ምድርን የፈጠረ ቃል

በግርግም ተኛ በትሕትና

ክብሩን ትቶ ወደ እኛ ወረደ

ፍቅር እንዲህ ነው የሚገለጠው

ስብሐት ለእግዚአብሔር በአርያም

ሰላም በምድር ለሰው ልጆች

የገና ብርሃን ፈንጥቋል ዛሬ

እንሂድ እንስገድ ለተወለደው

ምንጭ፦ ግጥሙ ለ Lyriqa በቀጥታ የቀረበ/የተዘጋጀ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ