በማለዳ
Bemaleda
ትራክ 1 · 5:58 · አማርኛ
መግቢያ · Intro
የተገባህ ምስጋና አንተ ነህ የኔ ጌታ
የተገባህ ክብር ላንተ ነው የኔ ጌታ
በምስጋና ወደፊትህ እቀርባለሁ ላመልክህ
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ይገባሃልና ለስምህ
ቁጥር 1 · Verse 1
በምስጋና የተፈራህ ገናና አምላክ ነህ
ለዑል አምላክ ብንዘምርህ ብንሰግድልህ አይበቃህም
አእላፋት ያንተ ፍጥረት ላንተ ክብር ያዜማሉ
ቀን ከለሊት ያንተን ስራ በምስጋና ያውጃሉ
አዝማች · Chorus ×2
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ
በቀትርም/በሌሊትም ዝማሬዬን አበዛለሁ አበዛለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ስምህ ሀያል የአማልክቱም አምላክ ገዢ ነህ
ታላቅ ጌታ የሆነልህ ሰማይ ምድሩ ምስጋናህ
መላዕክቱ ላንተ ሞገስ ላንተ ግርማ ይዘምራሉ
ባይገልፅህም በአዲስ ቅኔ ምስጋናህን ያውዳሉ
አዝማች · Chorus ×2
በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ
በቀትርም/በሌሊትም ዝማሬዬን አበዛለሁ አበዛለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ለኔ ብዙ ተደርጎልኛል/ሆኖልኛል ኧረ አኔ ብዙ ሆኖልኛል/ተደርጎልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይሻለኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይበጀኛል
ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅልኛል /x፪
መዝጊያ · Outro
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን
እግዚአብሔርን ያመስግን /x፬
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ