Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልተረሳሁም

Alteresahum

ትራክ 9 · 7:42 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አልተረሳሁም ባንተ ዘንድ ከቶ አጠወኝም ከመንገድ

የሁልጊዜ ነው ወዳድነትህ አትለወትም ሁኔታን አይተህ

ታውቀኛለህ አንተ በስመ ከቶ አተወኝም

አትረሳኝም አንተ ሰውን ከቶ አትጥልም

በዚህ እፅናናለሁ አንተን አይሀለሁ

በዚህ እፅናናለሁ በረታለሁ አንተን ብቻ አይሀለሁ

ኢየሱስ የልቤ ጌታ ዉስጤን አዋቂ

እየሱስ ባገኘኝ ሁሉ ልቤን ጠባቂ

ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ የልቤ ብርታት

የመኖር አቅሜ የልቤ ጠገን የልቤ ፅናት

የለኝም የምመካበት/ የምፅናናበት ልቤን የማስተጋበት/የምጥልበት

የዉስተን አንተ ታውቃለህ/ታያለህ ልቤን ትደግፋለህ

እየሱስ ያልተፈጠሩ ቀኖቼን ያየህ

እየሱስ ያሰፈርካቸው በክብር ፅፈህ

አምናለሁ ለኔም እንዲህ ነህ አትዘነጋኝም

በእጆቺህ መዳፍ የቀረፅከኝን አትረሳኝም

ከመዳፍህ ካልተፋሁ ካወቀኝ ይበቃኛል

የተረሳሁ ሲመስለኝ መንፈስህ ያፀናኛል

ካይኖቺህ ፊት ውላለሁ እንደብዙ ሆናለሁ

ታውቀኛለህ በስሜ ሁሉን ባንተ እረሳለሁ

እፅናናለሁ ፊትህን ሳይ እበረታለሁ ፊትህን ሳይ

ቀና እላለሁ ፊትህን ሳይ እበረታለሁ አይንህን ሳይ

የለኝም የምመካበት/ የምፅናናበት ልቤን የማስተጋበት/የምጥልበት

የዉስተን አንተ ታውቃለህ/ታያለህ ልቤን ትደግፋለህ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ