Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቤዛ ሆነልን

Beza Honelen

2012 · ትራክ 3 · 8:25 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንዲህ ተብሎ አይነገር የጌታ ምህረት

ለሰው ልጅ የሆነው ነገር በመስቀሉ ሞት (፪x)

ቤዛ ሆነልን በመሃል ገብቶ

ከሞት አዳነን ስለ እኛ ሞቶ (፪x)

በጎልጎታ የፈሰሰው ደሙ እኔን ለማዳን ነው

ፍቅሩን በሞት የገለጠው የታደገኝ ኢየሱስ ነው

ፍቅሩን በሞት የገለጠው የታደገኝ ኢየሱስ ነው

(እየሱስን ነው) ቤዛዬ ያልኩት

(እየሱስን ነው) ምትኬ ያልኩት

(እየሱስን ነው) ህይወቴ ያልኩት

(እየሱስን ነው) አዳኜ ያልኩት

በመስቀል ላይ ሃጥያቴን

ተሸክሞ ሞተ ሞቴን

ዛሬ በህይወት የምኖረው

በሰራልኝ ውለታ ነው (፪x)

(እየሱስን ነው) ቤዛዬ ያልኩት

(እየሱስን ነው) ምትኬ ያልኩት

(እየሱስን ነው) ህይወቴ ያልኩት

(እየሱስን ነው) አዳኜ ያልኩት

አመልከዋለሁ ሁልጊዜ

ቤዛ ሆኗታል ለነፍሴ (፪x)

ኢየሱሴ አዳኝ ለነፍሴ

ኢየሱሴ ቤዛ ለነፍሴ

ኢየሱሴ አዳኝ ለነፍሴ

ኢየሱሴ ቤዛ ለነፍሴ

(እየሱስን ነው) ቤዛዬ ያልኩት

(እየሱስን ነው) ምትኬ ያልኩት

(እየሱስን ነው) ህይወቴ ያልኩት

(እየሱስን ነው) አዳኜ ያልኩት

የሃጢያት እዳ የከበደኝ

በጨለማ የተዋጥኩኝ

ሆኜ ሳለው እኔ እስረኛ

ኢየሱሴ ሞተልኛ

በርሱ መሞት ህያው ሆንኩኝ

ከዘላለም ጥፋት ዳንኩኝ

(እየሱስን ነው) ቤዛዬ ያልኩት

(እየሱስን ነው) ምትኬ ያልኩት

(እየሱስን ነው) ህይወቴ ያልኩት

(እየሱስን ነው) አዳኜ ያልኩት

ለምን እንደወደድከኝ ባይገባኝም

ይህንን አውቃለው ይህንን

ስለ እኔ ሞተህ በህይወት መኖሬ

ለዘለአለም ልጅህ መባሌ (፪x)

አይቻለው ምህረትህን

አይቻለው ልዩ ፍቅርህን

ማን እንዳንተ ይሆናል

ማንስ ልብን ይረዳል

ለእኔስ ሁሉን ሆንክልኝ

ጌታ በአንተ አማረብኝ (፪x)

ማዕረጌ ነህ ለዘለዓለም

ትምክቴ ነህ ለዘለዓለም

ጋሻዬ ነህ ለዘለዓለም

ትምክቴ/ውበቴ ነህ ለዘለዓለም (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ