Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በምህረትህ ተከልዬ

Bemehereteh Tekeleyie

2012 · ትራክ 1 · 4:37 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በምህረትህ ተከልዬ

አልፌአለው ሁሉን ችዬ

ስላለኸኝ ዋስትናዬ

ከቶ አልፈራም የነገዬን

በጨለመው(ባስጨናቂው) ሌሊት ያኔ አሳልፈኽ

ቀን ካወጣህልኝ እንባዬን አብሰኽ

ነገን እንዴት ልፍራ ልስጋ ለመኖሬ

አንተ እያለኸኝ የዘላለም ክብሬ

እንካ ምሥጋናዬን እንካ (፫x)

እንካ አምልኮዬን እንካ (፫x)

እንካ ሽብሸባዬን እንካ (፫x)

እንካ ዕልልታዬን እንካ (፫x)

ይገባሃልና ጌታ ይገባሃልና

ይገባሃልና ኢየሱስ ይገባሃልና

በምህረትህ ተከልዬ

አልፌአለው ሁሉን ችዬ

ስላለኸኝ ዋስትናዬ

ከቶ አልፈራም የነገዬን

ጠላት በዙሪያዬ ቢያገሳ እንዳንበሳ

ከለላዬን ሳይ ቢጮህ ቢያገሳ

የሰማዩ አባቴ እኔን ከልሎኛል

ክፉ አንዳያገኘኝ ቅጥር ቀጥሮልኛል

እንካ ምሥጋናዬን እንካ (፫x)

እንካ አምልኮዬን እንካ (፫x)

እንካ ሽብሸባዬን እንካ (፫x)

እንካ ዕልልታዬን እንካ (፫x)

ይገባሃልና ጌታ ይገባሃልና

ይገባሃልና ኢየሱስ ይገባሃልና

በምህረትህ ተከልዬ

አልፌአለው ሁሉን ችዬ

ስላለኸኝ ዋስትናዬ

ከቶ አልፈራም የነገዬን

ባሸናፊው ጌታ ሁሉን ነገር ጥዬ

በመንፈሱ ብርታት ቆምኩኝ ቀና ብዬ

በሃይሌ አይደለም ወይም በብርታቴ

ያቆመኝ ጌታ ነው የሆነኝ ጉልበቴ

እንካ ምሥጋናዬን እንካ (፫x)

እንካ አምልኮዬን እንካ (፫x)

እንካ ሽብሸባዬን እንካ (፫x)

እንካ ዕልልታዬን እንካ (፫x)

ይገባሃልና ጌታ ይገባሃልና

ይገባሃልና ኢየሱስ ይገባሃልና

በምህረትህ ተከልዬ

አልፌአለው ሁሉን ችዬ

ስላለኸኝ ዋስትናዬ

ከቶ አልፈራም የነገዬን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ