ኧረ እንዳንተ
Ere Endante
2012 · ትራክ 2 · 4:38 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኧረ እንዳንተ ኧረ ማን አለ
ኧረ ልዩ ነህ ፍቅር ልበልህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እናት እንኳን ልጇን ትረሳ ይሆናል
ጓደኛም ወዳጅም አንድ ቀን ይከዳል
አንተ ግን አትከዳም ለዘለዓለም ነህ
ከእስትንፋሴ ይልቅ ለእኔ እጅግ ቅርብ ነህ
አዝማች · Chorus
ኧረ እንዳንተ ኧረ ማን አለ
ኧረ ልዩ ነህ ፍቅር ልበልህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከእናቴ ማህፀን ለራስህ የለየኸኝ
ከፊት እየቀደምክ እኔን የመራኸኝ
እጆቼን እየያዝክ ክፉን ያሳለፍከኝ
እግዚአብሔር አንተ ነህ በእውነት የወደድከኝ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ቢባል እንዳንተ ማነው
ወዳጅ ቢባል እንዳንተ ማነው
አባት ቢባል እንዳንተ ማነው
ረዳት ቢባል እንዳንተ ማነው
አንተ ብቻ ለእኔ የቅርብ ወዳጄ
አንተ ብቻ ለእኔ የልብ ወዳጄ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደ ሰው አይምሮ መቼ እኖራለሁ
ግን አንተ ይዘኸኝ ዛሬን አይቻለሁ
ለነገም አልፈራም በእጁ ውስጥ ነኝ
አመልካለሁ አንተን አባት ስለሆንከኝ
አዝማች · Chorus
ፍቅር ቢባል እንዳንተ ማነው
ወዳጅ ቢባል እንዳንተ ማነው
አባት ቢባል እንዳንተ ማነው
ረዳት ቢባል እንዳንተ ማነው
አንተ ብቻ ለእኔ የቅርብ ወዳጄ
አንተ ብቻ ለእኔ የልብ ወዳጄ (፪x)
ኧረ እንዳንተ ኧረ ማን አለ
ኧረ ልዩ ነህ ፍቅር ልበልህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ