Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ድሉ የጌታችን ነው

Delu Yegietachen New

2012 · ትራክ 10 · 4:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ድሉ የጌታችን ነው

ድሉ የአምላካችን ነው ድሉ

ድሉ የጌታችን ነው

ጠላትን ረገጠ አርነት አወጀ

ለእኛ ለልጆቹ ማረፊያ አዘጋጀ

ድሉ የአምላካችን ነው

ከዲያብሎስ ወጥመድ እንድንድን

በጌታችን ብርታት ተሞላን

እንግዲህ እንደ እንሰሳ አንተኛም

የኢየሱስ ነን እኛ

ድሉ የጌታችን ነው

ድሉ የአምላካችን ነው ድሉ

ድሉ የጌታችን ነው

ጠላትን ረገጠ አርነት አወጀ

ለእኛ ለልጆቹ ማረፊያ አዘጋጀ

ድሉ የአምላካችን ነው

እስራኤልን ከግብጽ ያወጣ

ፈርዖንን በባሕር የቀጣ

ይህንን ታዳጊ አምላክ ታምነናል

በድል ይመራናል

ድሉ የጌታችን ነው

ድሉ የአምላካችን ነው ድሉ

ድሉ የጌታችን ነው

ጠላትን ረገጠ አርነት አወጀ

ለእኛ ለልጆቹ ማረፊያ አዘጋጀ

ድሉ የአምላካችን ነው

ኢያሱ ጌዲዮንና ዳዊት

አብርሃምና ሙሴ አለፉ

የእምነትና የጦር አርበኞች

የደም ምሳሌዋች

ድሉ የጌታችን ነው

ድሉ የአምላካችን ነው ድሉ

ድሉ የጌታችን ነው

ጠላትን ረገጠ አርነት አወጀ

ለእኛ ለልጆቹ ማረፊያ አዘጋጀ

ድሉ የአምላካችን ነው

የጠላት ማሽካካት ድንፋታ

የሰልፍ የጦር ብዛት ጋጋታ

ለኃያሉ ኢየሱስ ምንድን ነው

ሁሉም በእጁ ነው

ድሉ የጌታችን ነው

ድሉ የአምላካችን ነው ድሉ

ድሉ የጌታችን ነው

ጠላትን ረገጠ አርነት አወጀ

ለእኛ ለልጆቹ ማረፊያ አዘጋጀ

ድሉ የአምላካችን ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ