Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከመቃብር ወዲያ

Kemeqaber Wediya

2012 · ትራክ 15 · 3:02 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከመቃብር ወዲያ ማን ይከተለኛል

ዝናም ይከዳኛል ሃብትም ይተወኛል ጊዜም ይረሳኛል

ሁሉም ይቅር ኢየሱስ ያዋጣናል

ሃብቴም አሁን ያልፋል

ቁመናም እንድ ቀን ይጥለኛል

ሁሉም ይጥላል

የጌታዬ ዝና ዘላቂ ነውና

ፍቅር ባለዝና

ከመቃብር ወዲያ መጠለያ (፪x)

ከመቃብር ወዲያ ማን ይከተለኛል

ዝናም ይከዳኛል ሃብትም ይተወኛል ጊዜም ይረሳኛል

ሁሉም ይቅር ኢየሱስ ያዋጣናል

እውነትን አውቂ ጥበበኛ

ወይም ድሃ ብሆን ችግረኛ

ዝናዬ ነው የሚያልፈኝ

ሆኘ በዚህ ብገኝ

ከሞት ወዲህ ወዲያ

ካለአምላኬ ዝና

የላትማ በዚያ ነፍሴ መጠለያ (፪x)

ከመቃብር ወዲያ ማን ይከተለኛል

ዝናም ይከዳኛል ሃብትም ይተወኛል ጊዜም ይረሳኛል

ሁሉም ይቅር ኢየሱስ ያዋጣናል

ከሞት ወዲያ ማዶ ድል አድራጊ

ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ታዳጊ

በሞት ጣል ሼድ አንድም ነገር አልያዝኩኝም

ሁሉን ነገር ትቻለሁ በእየሱስ አርፋለሁ (፪x)

ከመቃብር ወዲያ ማን ይከተለኛል

ዝናም ይከዳኛል ሃብትም ይተወኛል ጊዜም ይረሳኛል

ሁሉም ይቅር ኢየሱስ ያዋጣናል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ