Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ደረሰልኝ

Dereselegn

2013 · ትራክ 1 · 4:40 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አዬ

ደረሰልኝ ተራዬ

ደረሰልኝ ተራዬ

ላንሳ በገናዬን (፪x)

ደረሰልኝ ተራዬ

ደረሰልኝ ተራዬ

ላንሳ በገናዬን (፪x)

እባቡን ጊንጡንም አየረጋገጠ

አስማቱን መተቱን ድግምቱን ሟርቱን እየገለበጠ (አሄ)

እለፍ አለኝ ጌታ መንገዴን ከፋፍቶ

የሚያስፈራራውን ጠላቴንም መቶ

እለፍ አለኝ ጌታ መንገዴን ከፋፍቶ

የሚያስፈራራውን ጠላቴንም መቶ

በሞትና በእኔ አንድ እርምጃ ቀርቶ

ጌታም ከመሻሸ መጥቶ

የቀደመኝ መስሎት ከፊት ፊት የሮጠው

ዘግይቶ የመጣ አምላኬ ቀደመው (፪x)

ቀደመው አሆ (፬x)

ቀደመው አሆ (፬x)

ደረሰልኝ ተራዬ

ደረሰልኝ ተራዬ

ላንሳ በገናዬን (፪x)

ደረሰልኝ ተራዬ

ደረሰልኝ ተራዬ

ላንሳ በገናዬን (፪x)

እባቡን ጊንጡንም አየረጋገጠ

አስማቱን መተቱን ድግምቱን ሟርቱን እየገለበጠ (አሄ)

እለፍ አለኝ ጌታ መንገዴን ከፋፍቶ

የሚያስፈራራውን ጠላቴንም መቶ

እለፍ አለኝ ጌታ መንገዴን ከፋፍቶ

የሚያስፈራራውን ጠላቴንም መቶ

አልተኛም ለሰይጣን እንቅልፍ አይወስደኝ

መንገድ ላይ ሊያስቀረኝ ለሚተጋብኝ (፪x)

ይፈልጋል እንጂ ከመንገድ ሊያስቀረኝ

ጠላቴ የማይደፍረው ብርቱ ቅጥር አለኝ

ይፈልጋል እንጂ ከመንገድ ሊያስቀረኝ

ጠላቴ የማይደፍረው ብርቱ ቅጥር አለኝ

ብርቱ ነህ አሆ (፫x)

ብርቱ ቅጥር አለኝ

ብርቱ ነህ አሆ (፫x)

ብርቱ ቅጥር አለኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ