እጠብቅሃለሁ
Etebeqehalehu
2013 · ትራክ 2 · 5:13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ነገ መልካም ይሆናል
እያልኩኝ በተስፋ እኖራለሁ
ግራ ቀኝ አላይም እጠብቅሃለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ግን ለምን አልገባኝም
ስጠራህ ዝም አልከኝ
የዓይኖቼ እምባ እስኪፈስ
ለምኜ ተው ተመለስ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በመንፈቅ ሌሊት ከአልጋዬ ወርጄ
ሚስጢሬን ነገርኩህ ፊትህ ተደፍቼ
እንግዲህ ሁሉንም በአድራሻ ልኬያለሁ
እኔም በአድራሻዬ እጠብቅሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ከሰዎች ደብቄ ለአንተ የነገርኩህ
እንዴት አደረክልኝ ያጫወትኩህን
ዛሬም ነገም እጠብቅሃለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ድንገት ትመጣለህ ይህን አውቃለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ዓመታት ሲሄዱ በጥያቄዬ ላይ
የተውከው መሰለኝ ታክቶ የእኔ ጉዳይ
ዛሬ ቢሆን ነገ እታገስሃለሁ
ልትረዳኝ ስትመጣ ድንገት አይሃለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ከሰዎች ደብቄ ለአንተ የነገርኩህ
እንዴት አደረክልኝ ያጫወትኩህን
ዛሬም ነገም እጠብቅሃለሁ
ቁጥር 6 · Verse 6
ድንገት ትመጣለህ ይህንን አውቃለሁ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
አይሃለሁ ስትደርስልኝ
አይሃለሁ ስትመጣልኝ
አይሃለሁ መልሴንም ከላይ
አይሃለሁ ስትልክልኝ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ