እኔም ወግ አየሁ እንደሰው
Eniem Weg Ayehu Endesew
2011 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አዝ፥ (እኔም ወግ አየሁ እንደሰው
እኔም ክብር አየሁ እንደሰው
እንደ ሰው /2/)x2
እኔም ወግ አየሁ እንደ ሰው
ለአምላክ ምስጋና ይድረሰው
(ክበር ልበል በተራዬ
ንገስ ልበል በተራዬ
ኢየሱስ ጌታዬ) 2
ቁጥር 1 · Verse 1
ክበር ልበል በተራዬ
ቀን አወጣልኝ ጌታዬ
ሰላሳ ስምንት ዓመታት ሙሉ
የአልጋ ቁራኛ ሽባ መባሉ
መኖር ሰልችቶኝ ሞቴን ስጣራ
እኔም ልታሰብ ደረሰኝ ተራ
አልጋህን ይዘህ ተነስ ሂድ አለ
ከልካይ ማን አለ
ደርቆ የኖረው ያ ፊቴ ወዛ
ሞገሴ በዛ
ሞቴን ለሞተልኝ ባለውለታዬ
አልጥልህም ላለኝ ባለውለታዬ
አለሁልህ ላለኝ ባለውለታዬ
ገና ይዘመራል ከዚህም በላይ
አዝማች · Chorus
አዝ፣ እኔም ወግ አየሁ እንደ ሰው...
በቤተ መቅደስ በመልካሟ ደጅ
ስለምን ሳለሁ ምጽዋት ከሰው እጅ
አንካሳን አይቶ ሊፈውስ ወዶ
የእግዚአብሔር መንፈስ በጴጥሮስ ወርዶ
በኢየሱስ ስም ተነሳ አለ
ከልካይ ማን አለ
ደርቆ የኖረው ያ ፊቴ ወዛ
ሞገሴ በዛ
ሞቴን ለሞተልኝ ባለውለታዬ
አልጥልህም ላለኝ ባለውለታዬ
አለሁልህ ላለኝ ባለውለታዬ
ገና ይዘመራል ከዚህም በላይ
ቁጥር 2 · Verse 2
አዝ፣ እኔም ወግ አየሁ እንደ ሰው...
የጤሜዎስ ልጅ በርጠሜዎስ ነኝ
ስድቡ ንቀቱ ቀለብ የሆነኝ
አትጩህ የሚል ከልካይ ቢነሳ
እድሜ የፈጀውን ጭንቄን አልረሳ
ኢየሱሴ ግን ጥሩልኝ አለ
ከልካይ ማን አለ
ደርቆ የኖረው ያ ፊቴ ወዛ
ሞገሴ በዛ
ሞቴን ለሞተልኝ ባለውለታዬ
አልጥልህም ላለኝ ባለውለታዬ
አለሁልህ ላለኝ ባለውለታዬ
ገና ይዘመራል ከዚህም በላይ
ቁጥር 3 · Verse 3
አዝ፣ እኔም ወግ አየሁ እንደ ሰው...
ለተበደሉት በቅን የሚፈርድ
አባብሎ የሚይዝ በፍቅር በውድ
ያለቀን ነገር መቀጠል የሚያውቅ
ምስኪን የማይንቅ አምላኬ ትልቅ
ይህንን አምላክ ያመለካችሁ
ይኩራ ልባችሁ
አቤት ብርታቱ አቤት ችሎቱ
የጌትነቱ
ሞቴን ለሞተልኝ ባለውለታዬ
አልጥልህም ላለኝ ባለውለታዬ
አለሁልህ ላለኝ ባለውለታዬ
ገና ይዘመራል ከዚህም በላይ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ