እረኛዬ
Eregnaye
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ
የነፍሴ ጠባቂ አንተ የማትተኛ
እኮራለሁ ባንተ እመካለሁ
በምንም አልፈራም በምንም አልሰጋም
የነፍሴ ንጉስ ኢየሱስ አንተ ለኔ እረኛዬ ነህ
ነፍሴን ከአዳኝ ወጥመድ ዘወትር ትጠብቀኛለህ
አንተ የኔ እረኛ አትተኛም አታንቀላፍም
በሰላም ውዬ አድራለሁ እኔ በምንም አልሰጋም
አዝማች · Chorus
እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ………
ቁጥር 2 · Verse 2
ካንተ ሌላ ወዳጅ ካንተ ሌላ እረኛ
ለኔስ ምንም የለኝ አንተ የማትተኛ
መልካም እረኛ ኢየሱስ ስለኔ ነፍሱን ሰጥቶኛል
ሰላሙ ልቤን ሞልቶ በድል ያራምደኛል
አዝማች · Chorus
እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ………
ቁጥር 3 · Verse 3
በለመለመ መስክ ዘወትር ያሳድረኛል
በእረፍት ውሀ ዘንድ ጌታ እኔን ይመራኛል
ቸርነት ምህረቱ እየተከተሉኝ
ከክፉ ይጠብቁኛል በድል ያራምዱኛል
አዝማች · Chorus
እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ………
ቁጥር 4 · Verse 4
ምድር ብትነዋወጥ ብትነዋወጥ
ሁሉም ነገር ስፍራውን ቢለቅ
ከቶ እንዳልፈራ ከቶ እንዳልናወጥ
ልቤን ሞላኸው በሰላም በእረፍት
ያረጋጋኸኝ በነውጡ አለም
ጋሻዬ ነህና ለዘለአለም
እኔ ልበልህ እረድኤቴ
ስለሆንክልኝ አቅም ጉልበቴ
እልሀለሁ እረድኤቴ(6x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ