ለአምላክነትህ
LeAmlaknetih
አማርኛ
አዝማች · Chorus
ላምላክነትህ እንሰግዳለን
ለጌትነትህ እንዘምራለን
ክቡር ክቡር ክቡር ነህና
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህና (2X)
ቁጥር 1 · Verse 1
ለኛስ ውለታህ ስለበዛብን
የማይገባንን ከፍ ክፍ ካረከን
በልጅህ ምክንያት ወዳንተ ቀርበናል
ክቡር ነህ እግዚአብሔር ተመስገን ብለንሀል (2X)
አዝማች · Chorus
ላምላክነትህ እንሰግዳለን
ለጌትነትህ እንዘምራለን
ክቡር ክቡር ክቡር ነህና
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህና (2X)
ቁጥር 2 · Verse 2
በላይ በሰማይ ተቀምጠህ ላለህው
ብርሃንን እንደልብስ ለተጎናጸፍከው
በእውነት በመንፈስ እንሰግድልሃለን
ስምህን በዝማሬ እንወድሰዋለን
የፈጠርካቸውም አንተን ይጠሩሀል
ጠዋትና ማታ ክብርን ይሰጡሀል
አሁንም ተባረክ ስምህ ይባረክ
በእጆችህ ስራ ዛሬም ተወደስ
አዝማች · Chorus
ላምላክነትህ እንሰግዳለን
ለጌትነትህ እንዘምራለን
ክቡር ክቡር ክቡር ነህና
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህና (2X)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ