እስክትመጣ
Eskitimeta
ትራክ 5 · 4:30 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በክብር ወዳረግከው አሳባችን እየሄደ
መዝገባችን ወዳለበት ልባችን እየነጎደ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን ማራናታ እየሱስ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን አትመጣም ወይ እየሱስ
ቁጥር 2 · Verse 2
የመለከት ድምፅ እስክንሰማ
ስትወርድ ልናይህ በክብር በደመና
በጥልቅ ናፍቆት ወደላይ እናያለን
መሲሃችን ሆይ እባክህ ቶሎ ናልን
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን ማራናታ እየሱስ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን አትመጣም ወይ እየሱስ
አዝማች · Chorus
አሜን ቶሎ ና የኛ ጌታ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ጌታ እየሱስ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ማራናታ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ጌታ እየሱስ ቶሎ ና
ቁጥር 3 · Verse 3
ከሙታን መንደር ልጆችህን የጠራህ
የንጋት ኮከብ ለጠፋነው የበራህ
በመደላደል ረስተንህ አንቀመጥ
መዳኒታችን ዳግመኛ እስክትገለጥ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን ማራናታ እየሱስ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን አትመጣም ወይ እየሱስ
አዝማች · Chorus
አሜን ቶሎ ና የኛ ጌታ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ጌታ እየሱስ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ማራናታ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና ጌታ እየሱስ ቶሎ ና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ