እወድሃለሁ
Ewedehalehu
2002 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ሕይወቴን ሁሉ ለአንተ ሰጥቻለሁ (፪x)
አንተን አንተን ይላል ልቤ ይፈልግሃል
በፍፁም መደነቅ መገረም ተሞልቷል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ትናንትናም ዛሬም ነገም
እስከ ዘለዓለም አንተ ነህ
ጌታ ኢየሱስ አቻ የለህም
ጥንትም ጌታ ነህ
ጥንትም ኃያል ነህ
አቻ የሌለህ
ጥንት ቢሆንም ዬሃ
ዛሬ ቢሆንም ዬሃ
ያው ነው ሁሌም ዬሃ (፪x)
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ሕይወቴን ሁሉ ለአንተ ሰጥቻለሁ (፪x)
አንተን አንተን ይላል ልቤ ይፈልግሃል
በፍፁም መደነቅ መገረም ተሞልቷል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቅን ፍፁም አይለወጥም
እንደ ትናንትም ዛሬ ይኖራል እስከ ዘለዓለም
ሰው አይደለህም ወረት አታውቅም አትቀየርም
ጥንት ቢሆንም ዬሃ
ዛሬ ቢሆንም ዬሃ
ያው ነው ሁሌም ዬሃ (፪x)
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ሕይወቴን ሁሉ ለአንተ ሰጥቻለሁ (፪x)
አንተን አንተን ይላል ልቤ ይፈልግሃል
በፍፁም መደነቅ መገረም ተሞልቷል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወድሃለሁ ወድሃለሁ ወድሃለሁ
ሁልጊዜ በሕይወቴ አመልክሃለው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ