ሰማይና ምድር
Semayena Meder
2002 · ትራክ 2 · 6:56 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በሰማይና በምድር በውስጡ ያለውን ነገር
አስበህ ይሰራሃቸው አንተ ነህ እኮ እግዚአብሔር
እጅጉን በጣም ይገርማል ጥበብህ ጌታ ያስደንቃል
አቤት ዕውቀትህ ስራህ ሊወራልውህ/ሊነገርልህ ይገባህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤት (፬x)
ስለ ስጦታህ ምሕረትህ ተመስገን ስለ ጥበቃህ
ስጦታህ ደስ ያሰኛል ልብን ይማርካል
አንተን የሚመስል ኧረ ከየት ይገኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይና በምድር በውስጡ ያለውን ነገር
አስበህ ይሰራሃቸው አንተ ነህ እኮ እግዚአብሔር
እጅጉን በጣም ይገርማል ጥበብህ ጌታ ያስደንቃል
አቤት ዕውቀትህ ስራህ ሊወራልውህ/ሊነገርልህ ይገባህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አቤት (፬x)
ስለ ስጦታህ ምሕረትህ ተመስገን ስለ ጥበቃህ
የምንተነፍሰው ሳንከፍልበት ዋጋ
ሰጥተኸን እያየን ነውና የአንተን ፀጋ (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይና በምድር በውስጡ ያለውን ነገር
አስበህ ይሰራሃቸው አንተ ነህ እኮ እግዚአብሔር
እጅጉን በጣም ይገርማል ጥበብህ ጌታ ያስደንቃል
አቤት ዕውቀትህ ስራህ ሊወራልውህ/ሊነገርልህ ይገባህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤት (፬x)
ስለ ስጦታህ ምሕረትህ ተመስገን ስለ ጥበቃህ
ዓለማትን በቃልህ ፈጠርህ አፀናህ
ለሰው ልጅ መልካም ነገር አበጀህ (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይና በምድር በውስጡ ያለውን ነገር
አስበህ ይሰራሃቸው አንተ ነህ እኮ እግዚአብሔር
እጅጉን በጣም ይገርማል ጥበብህ ጌታ ያስደንቃል
አቤት ዕውቀትህ ስራህ ሊወራልውህ/ሊነገርልህ ይገባህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አቤት (፬x)
ስለ ስጦታህ ምሕረትህ ተመስገን ስለ ጥበቃህ
የተራራ የወንዙ የባሕር የውቂያኖስ
ፈጣሪ አንተ እኮ ነህ ለዘለዓለም ንገሥ (፪x)
አዝማች · Chorus
በሰማይና በምድር በውስጡ ያለውን ነገር
አስበህ ይሰራሃቸው አንተ ነህ እኮ እግዚአብሔር
እጅጉን በጣም ይገርማል ጥበብህ ጌታ ያስደንቃል
አቤት ዕውቀትህ ስራህ ሊወራልውህ/ሊነገርልህ ይገባህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ