Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እውነተኛ ሰላም

Ewnetegna Selam

2012 · ትራክ 1 · 7:01 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እውነተኛ ሰላም እውነተኛ ደስታ

የገባኝ አሁን ነው አንተን ስይዝ ጌታ

ብዙ ተቅበዘበዝኩ ደህንነት ፍለጋ

በማመኔ ብቻ ላገኘው አንተ ጋ

ምቾቴ አንተ ነህ

ሰላሜ አንተ ነህ

እረፍቴ አንተ ነህ

ልቤ ያረፈብህ (፪x)

ልቤ ያረፈብህ (፬x)

(ያረፈብህ (፰x))

ወርቅ ዕንቁ ቢሞላ ላይሰጠኝ ሰላም

ዕውቀት ቢደረደር አያሳርፍም

ነፍሴ ስትጨነቅ ጥያቄዋ በዝቶ

መመለስ የሚችል ከወዴት ተገኝቶ

አንተ ስትገባ ወደ ሕይወቴ

ተለዋወጠ ማንነቴ

ጥያቄ ሁሉ ተመለሰ

ሰላም ደስታ በውስጤ ፈሰሰ (፪x)

በለስ ባታበቅል ፍሬዋ ባይገኝ

ምድራዊ ነገሬ ቢጨላልምብኝ

ቢጐድል ቢሞላ እኔ አልገረምም

በዚህ ሁሉ መሃል ሰላሜ አይጐልም

የማዳኑን ክንድ አልብሶኛል

መጐናጸፊያን ደርቦልኛል

በአምላኬ ሃሴት አደርጋለሁ

ለዘለዓለም በደስታ ኖራለሁ (፪x)

እውነተኛ ሰላም እውነተኛ ደስታ

የገባኝ አሁን ነው አንተን ስይዝ ጌታ

ብዙ ተቅበዘበዝኩ ደህንነት ፍለጋ

በማመኔ ብቻ ላገኘው አንተ ጋ

ምቾቴ አንተ ነህ

ሰላሜ አንተ ነህ

እረፍቴ አንተ ነህ

ልቤ ያረፈብህ (፪x)

ልቤ ያረፈብህ (፬x)

የሚያውቁኝ በሙሉ እጅግ ተገረሙ

እንዲህ የሚያሳርፍ "ምን አገኘ?" እያሉ

ፍፁም መረጋጋት እርፍ ማለት

የትም አይገኝም በሌለህበት

ሁሉን ነገር ለአንተ ሰጥቼህ

ተደላደልኩኝ አረፍኩብህ

የማይለወጥ ፍቅርህ ሲነካኝ

ሌላው ሁሉ ከንቱ ሆነብኝ (፪x)

የደስታዬ ምንጭ ኢየሱስ

ሰላም የሆነኝ ኢየሱስ

ማንም ከእንግዲህ ኢየሱስ

የማይለያየኝ ኢየሱስ

ቁስሌን ፈውሶ ያረገኝ ደህና

አከብረዋለው ክብሬ ነውና (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ