ወዳጅ ማን አለ
Wedaj Man Ale
2012 · ትራክ 3 · 7:19 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የማይከዳ ትቶ የማይሄድ
ሃብት ንብረት ፊት አይቶ የማይወድ
እውነተኛ ወዳጅ ማን አለ
እንደ ኢየሱስ ያለ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ታናሽነቴን ያልናቀ እጁን ዘርግቶ ጠራኝ
እወድሃለሁኝ ልጄ አንተ የእኔ ነህ አለኝ
በስደት በባርነት አገር ታሪኬን በክብር ቀየረ
ብቻዬን ነኝ ባልኩበት ጊዜ ለካ ጌታ አብሮኝ ነበረ (፪x)
አዝማች · Chorus
(አይቻለሁ) ወዳጅ መስሎ ስንቱ ቀርቦኝ
(አይቻለሁ) ምድረ በዳ ሲሄድ ጥሎኝ
(አይቻለሁ) አንተ ግን ጌታ ስቲዘኝ
(አይቻለሁ) በድካሜ እንኳን ተሸከምከኝ
አዝማች · Chorus
አይለወጥ ፍቅርህ
አይሰለች ትክሻህ
የሚያልፈው ሁሉ ሲጸየፈኝ
ቁስሌን ጠራርገህ አነሳኸኝ
አይለወጥ ፍቅርህ
አይሰለች ትክሻህ
የሚያልፈው ሁሉ ሲጸየፈኝ
አባት አንተ ነህ የተጠጋኸኝ
አዝማች · Chorus
(አይለወጥ ፍቅርህ (፫x))
(አይሰለች ትክሻህ)
ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ወዳጄ
እኔስ አላየሁም እንደ ኢየሱስ የሚመች
ሁሉም በሸሸበት በዚያ በከባዱ ጊዜ
ኢየሱስ አይደለም ዎይ ያወጣኝ ከሃዘን ከትካዜ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አቤት የአንተስ ፍቅር አቤት ቸርነትህ
ለጠላትስ አይቀር በመስቀል መሞትህ
ልቤ አቅም አጣ በፍቅርህ ጉልበት
ተሸነፍኩኝ በቃ ገዛኝ ማንነትህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ማን ብዬ እጠራሃለሁ
ፍቅርህ ከምለው በላይ ነው
ኢየሱሴ ትለያለህ
እንደ አንተ ያለ ማን ወዳጅ አለ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ