ውበት እና ግርማህ
Webet Ena Germah
2012 · ትራክ 2 · 5:27 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ውበት እና ግርማህ ያማረ
ሞገስህ እጅግ የከበረ
ዝናህን ሰምቼ መጣሁ
ከሰማሁት በላይ ሆኖ አየሁ
አስገረመኝ አገዛዝህ
ሁሉን በፍቅር ይዘህ
አያልቅም ቢነገር ስራህ
ጌታዬ እጅግ ልዩ ነህ
ልዩ ነህ (፫x)
ጌታዬ እጅግ ልዩ ነህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአማልክት መካከል እንዳንተ ያለ ማነው
በላይ በሰማይ በታች በምድር
አንተን የሚመስል አጣሁ
ኃያልና የተፈራህ
ሥልጣናት ሁሉ በእጅህ ነው
መንግሥትህ ዘለዓለም
እጅግ የጸና ነው
ዝናህን አውርቼ አልጨርሰው
አይበቁኝምና ቃላት
ለመግለጽ የአንተን ማንነት
ስለዚህ ዝም ብዬ ላምልክ
ሕይወቴን ለአንተ ላስገዛልህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ውበት እና ግርማህ ያማረ
ሞገስህ እጅግ የከበረ
ዝናህን ሰምቼ መጣሁ
ከሰማሁት በላይ ሆኖ አየሁ
አስገረመኝ አገዛዝህ
ሁሉን በፍቅር ይዘህ
አያልቅም ቢነገር ስራህ
ጌታዬ እጅግ ልዩ ነህ
ልዩ ነህ (፫x)
ጌታዬ እጅግ ልዩ ነህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙ ኃያላን የነበሩ
ታላዝ ነን ብለው የተነሱ
ዛሬ ቢፈለጉ አንዳቸውም የሉ
ሞት አሸንፏቸው ተረሱ
አንተ ግን ያለህ የነበርህ
ለዘለዓለም ትኖራለህ
አልፋና ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ
የሚስተካከልህ የሌለህ
ስለ አንተ ዘምሬ መቼ/መች ጠገብኩ (፪x)
ሥምህን ጠርቼ አልረካሁ (፪x)
ያንስብሃል ኢሄ አይበቃህ (፪x)
ከዚም በላይ ክብር ይብዛልህ (፪x)
አይበቃህምና ልጨምር ገና
ከልቤ ይፍለቅ ብዙ ምሥጋና (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ