ኢየሱስ
Eyesus
2011 · ትራክ 2 · 3:52 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደ ሚፈስ ዘይት ነው ስምህ
በጨለማ ብርሃን መውጫ መንገድ ሰላም
ሆኖልኛል ስምህ በጭንቅ ቀን ድህነት (ኦ)
ነፍሴን ከሞት መልሷልና ከታሰርኩበት ፈቶኛል
ቀንበሬን ሰብሮ ያላየሁትን ነጻነት አሳየኝ ስምህ ይክበር
አዝማች · Chorus
ኦ ስምህ ልዩ ነው
ኦ እኔም ወደድኩት
ኦ ስጠራው ብውል
ኦ ከቶ አልጠግበውም
ቁጥር 2 · Verse 2
ከስሞች በላይ ነው ስምህ
ከሁሉም ይበልጣል ኃያል
ኦ ስጠራው ብውል
ኦ ከቶ አልጠግበውም
ድንቅ ልዩ ነው እሮጦ ማምለጫ
አላሳፈረኝም በጭንቀት ስጠራው
ስምህን ተማምኖ የከሰረ የለም ኃጢአቱ ተሽሯል
ኃይሌን አድሷል እንደ ንስር በክንፍ ከፍ ብያለው በስምህ ጉልበት
አዝማች · Chorus
ኦ ስምህ ልዩ ነው
ኦ እኔም ወደድኩት
ኦ ስጠራው ብውል
ኦ ከቶ አልጠግበውም
ቁጥር 3 · Verse 3
ከስሞች በላይ ነው ስምህ
ከሁሉም ይበልጣል ኃያል
ኦ ስጠራው ብውል
ኦ ከቶ አልጠግበውም
ድንቅ መካር ነው ልዩ
የሰላም አለቃ የዘለዓለም አባት
ሆሆሆሆ ሆሆሆሆ
የዘለዓለም አባት
አዝማች · Chorus
ኦ ስምህ ልዩ ነው
ኦ እኔም ወደድኩት
ኦ ስጠራው ብውል
ኦ ከቶ አልጠግበውም (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሆ ሆ ሆ ሆ እኔም ወደድኩህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ