ታስደንቀኛለህ
Tasdeneqegnaleh
2011 · ትራክ 1 · 4:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለቁጣ የዘገየ ምህረትህ ለዘለዓለም
ለትውልድ ትውልድ የሚያልፍ ነው ታማኝነትህ
ፍቅርህ ወሰን የለውም ማለቂያ ዳርቻህ
ነፍሴ ታዜማለች እንዴት ግሩም ነህ
አዝማች · Chorus
አንተ ታስደንቀኛለህ አንተ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አጻሳትም በስራህ ፈለግ የለው መንገድህ
ከአይምሮ በላይ ከሰው ዕውቀት ነው ጥበብህ
አደራረግህ እጅግ ረቂቅ ፍፁም ጻድቅ
ነፍሴ ትቀኛለች እንዴት ዕጹብ ነህ
አዝማች · Chorus
አንተ ታስደንቀኛለህ አንተ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እምባዬን አብስክ ፍርሃቴን አራክ ኃጢአቴንም አጠብክ
ዛሬ ማውቀው ሁሉ በአንተ ነው ሁሉም በሁሉም ነህ
እምባዬን አብስክ ፍርሃቴን አራክ ኃጢአቴንም አጠብክ
ዛሬ ማውቀው ሁሉ በአንተ ነው ለእኔ ዓለሜ ነህ
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ ታስደንቀኛለህ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
(ፍቅር ፣ ሰላም ፣ እረፍት ፣ ቸር ፣ ታጋሽ ፣ መሃሪ)
አዝማች · Chorus
አንተ ታስደንቀኛለህ አንተ (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ካየሁህ ከሰማሁህ በላይ
ከለመድኩት በላይ
ሆንክብኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ