እዩልኝ
Eyulign
2021 · ትራክ 4 · 7:50 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እስቲ የኔን አምላክ እዩልኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እስቲ እግዚአብሔርን እዩልኝ (፪x)
እስቲ የኔን ጌታ እዩልኝ (፪x)
እስቲ ኢሄንን ውብ እዩልኝ (፪x)
እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ግን ሰው ሳያይህ እንዴት ያደንቅሃል
ሰው ሳያይህ እንዴት ያመልክሃል
ያወቅንህ ግን ማቆም አቅቶናል (፪x)
አዝማች · Chorus
እስቲ የኔን አምላክ እዩልኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስቲ ኢሄንን ውብ እዩልኝ (፪x)
እስቲ ኢሄንን ቆንጆ እዩልኝ (፪x)
እስቲ አለባበሱን እዩልኝ (፪x)
እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ውበት ያለው ክብር ያለው
ሞገስ ያለው ውበት ያለው
በሰው ብልሃት ያልተሰራ
አምላክ አለ ከእኔ ጋራ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እስቲ እግዚአብሔርን እዩልኝ (፪x)
እስቲ ኢህን መልካም እዩልኝ (፪x)
እስቲ ኢህንን ቸር እዩልኝ (፪x)
እስቲ የእኔን አምላክ እዩልኝ (፪x)
እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ
ቁጥር 6 · Verse 6
ነፍሴ ኮበለለች እርሱን ተከትላ
ሌላ ሌላ ነገር አልፈልግም ብላ (፪x)
እኔ አልፈልግም ብላ
አልፈልግም ብላ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
እስቲ የእኔን አምላክ እዩልኝ (፪x)
እስቲ ኢህን ጨዋ እዩልኝ (፪x)
እስቲ ኢህን ኃያል እዩልኝ (፪x)
እስቲ ኢህን ብርቱ እዩልኝ (፪x)
እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ
ቁጥር 8 · Verse 8
እኔማ በለሟል የአንተ አገልጋይ
በቤትህ ሰራተኛ ወዳጅ ልጅህ ነኝ
ባሪያህም እሆናለው በእኔ ፍላጐት
ጉልበቴን ዘመኔንም ተጠቀምበት
እኔማ እኔማ እኔማ እኔማ
እኔማ በለሟል የአንተ አገልጋይ
በቤትህ ሰራተኛ ወዳጅ ልጅህ ነኝ
ባሪያህም እሆናለው በእኔ ፍላጐት
ጉልበቴን ዘመኔንም ተጠቀምበት
ተጠቀምበት ተጠቀምበት ተጠቀምበት ተጠቀምበት
ቁጥር 9 · Verse 9
አቤቱ ውበትህ እጅግ ያስደንቃል
የፊትህን ብርሃን ማን አይቶ ይቆማል (፪x)
አምልኮና ስግደት ክብር ይገባሃል
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
እንዳንተ ያለ ውብ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
ቁጥር 10 · Verse 10
ነበልባል ዓይኖችህን
ያመረውን ፊትህን
የነጠረው እግርህን
እናውራው ውበትህን (፪x)
እንዳንተ ያለ ስላልተገኘ (፪x)
ፍጥረት ሊያደንቅህ ሊያይህ ተመኘ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ