ፍጠንልኝ
Fetenelegn
2012 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ህልምን ያሳየኸው ዮሴፍ ተጥሎ
ፍርድ ተጣሞበት በእስር ቤት ተረስቶ
አንተን የመጠበቅ ቢረዝምበት ጊዜው
ጠጅ አሳላፊው አታስበኝ አለው
ቀኑ ሲደርስ ግን በአንተ ተጐብኝቶ
በችኮላ ወጥቶ ጸሎቱ ተሰምቶ
አዝማች · Chorus
ተለመነኝ ጌታዬ ሆይ ተለመነኝ
ልመናዬ ወደ ጆሮህ ይድረስልኝ
ተለመነኝ አምላኬ ሆይ ተለመነኝ
ጸሎቴ ወደ ማደርያህ ይድረስልኝ(፪)
አዝማች · Chorus
አቤቱ ልቤ ጨከነ(፬)
እግዚአብሔር አለቴ ኃይሌ ነው እያለ
ሰው ምን ያደርገኛል ከእኔ ጋራ አለ
ልቤ ጨከነ
አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው(፬)
በአምላኬ በእግዚአብሔር ኃይሌን አድሳለሁ
ሰው ምን ያደርገኛል ጌታ ከእኔ ጋር ነው
ልቤ ጽኑ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ፊትህን የሚሹ በእኔ አይነወሩ
ተስፋ የሚያደርጉህ አይተውኝ አይፈሩ
በምሕረትህ ፊትህ አርግልኝ ጌታዬ
ጉብኝትህ ይፍጠን በቤትህ በአገሬ
ፍጠንልኝ ጌታዬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደምሕረትህ ብዛት ፍረድልኝ
ፍጠንልኝ አምላኬ ሆይ ፍጠንልኝ
እንደኃጢአቴ ከቶ አታርግብኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
አበቱ ልቤ ጨከነ(፬)
እግዚአብሔር አለቴ ኃይለ ነው እያለ
ሰው ምን ያደርገኛል ከእኔ ጋራ አለ
ልበ ጨከነ
አበቱ ልበ ጽኑ ነው(፬)
በአምላከ በእግዚአብሔር ኃይለን አድሳለሁ
ሰው ምን ያደርገኛል ጌታ ከእኔ ጋር ነው
ልበ ጽኑ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ