ክብሩ ለእግዚአብሔር
Kebru Legziabhier
2012 · ትራክ 3 · 5:20 · አማርኛ
ለቀብር ሲዘጋጅ ሰው ሬሳ ተብሎ
ትንሳኤ ሲሰጠው ሕይወት ተቀጥሎ
አንዳች እጣ አለበት የሰው ልጅ ብቃቱ
ሙታንን ላስነሳ ክብር ይሁንለቱ
ክብሩ ለእግዚአብሔር (፫x)
በባሪያዎቹ ላይ እየተገለጠ
በሽታን ከሕዝቡ ደዌን ለፈወሰ
ክብሩ ለእግዚአብሔር (፪x)
አምነዋለሁ ጌታን አምነዋለሁ (፪x)
ተዓምራትን በእጁ ሲሰራ ባይኔ አይቻለሁ
አምነዋለሁ ጌታን አምነዋለሁ
አውቀዋለሁ ጌታን አውቀዋለሁ (፫x)
ጠላቶቼን እንደገለባ ሲያቃጥላቸው
በዓይኔ አይቻለሁ ጌታን አውቀዋለሁ
የክፋቱ ሸንጐ በዘንዶ ሲመራ
ተገርስሶ ወድቆ ክቡር ሥም ሲጠራ
ደጋግመን ሰምተናል ተቃጥለናል ሲሉ
ነግቶለት ሲቦርቅ የመሸበት ሁሉ
ክብሩ ለእግዚአብሔር (፫x)
በሰማይም በምድሩ ለእርሱ ይሁን ክብሩ
ክብሩ ለእግዚአብሔር (፫x)
በሰማይም በምድሩ ለእርሱ ይሁን ክብሩ
ክብሩ ለእግዚአብሔር (፫x)
በሰማይም በምድሩ ለእርሱ ይሁን ክብሩ
ክብሩ ለእግዚአብሔር (፫x)
በሰማይም በምድሩ ለእርሱ ይሁን ክብሩ
በባሪያዎቹ ላይ እየተገለጠ
የቃሉን እምነት ለሕዝቡ አስተማረ
ክብሩ ለእግዚአብሔር
በባሪያዎቹ ላይ እየተገለጠ
ወንጌልን ለትውልድ ለዓለም ሰበከ
ክብሩ ለእግዚአብሔር
ለአያሌ ዘመዓት ህመም ያሰቃዩ
በባለ መድኃኒት መፍትሄ አላገኙ
ደዊው ተፈወሰ ወደ ኢየሱስ መጥቶ
ቀምበሩ ተሰብሮ ፍፁም ነጻ ወጥቶ
ሃኩሙ ኢየሱስ ነው (፫x)
በሽታውን ያዳነው ሃኪሙ ኢየሱስ ነው
ሃኩሙ ኢየሱስ ነው (፫x)
በሽታውን ያዳነው ሃኪሙ ኢየሱስ ነው
አምነዋለሁ ጌታን አምነዋለሁ (፪x)
ተዓምራትን በእጁ ሲሰራ ባይኔ አይቻለሁ
አምነዋለሁ ጌታን አምነዋለሁ
አውቀዋለሁ ጌታን አውቀዋለሁ (፫x)
ጠላቶቼን እንደገለባ ሲያቃጥላቸው
በአይኔ አይቻለሁ ጌታን አውቀዋለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ