ክብር ልለው አለሁ በፊቱ
Keber Lelew Alehu Befitu
2015 · ትራክ 8 · 4:38 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ዙፋኑንም ፍቅር የሞላው
በልጁ ደም እኔን ለገዛው (፪x)
ክብር ምስጋናዬ ይድረሰው
አዝማች · Chorus
ክበር ልለው አለሁ በፊቱ
ንገስ ልለው አለሁ በፊቱ
ግነን ልለው አለሁ በፊቱ (፪x)
ኃያል ክንደ ብርቱ
ቁጥር 2 · Verse 2
በገናዬን ላንሳ ጌታዬን ላወድስ
ስግደት ዝማሬዬ ከማደሪያው ይድረስ
ይገባዋል ለርሱ ኤልሻዳይ ነውና
ክብር ንገስ ልበል በመዝሙር በልልታ
አዝማች · Chorus
ክበር ልለው አለሁ በፊቱ
ንገስ ልለው አለሁ በፊቱ
ግነን ልለው አለሁ በፊቱ (፪x)
ኃያል ክንደ ብርቱ
ቁጥር 3 · Verse 3
በዘላለም ፍቅሩ እኔን የወደደኝ
በታላቅ ምረቱ በቤቱ ያቆመኝ
እንዳገለግለው ለርስቱ የለየኝ
የእግዚአብሔር ልጅ ልሆን ስልጣንን የሰጠኝ
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ዙፋኑንም ፍቅር የሞላው
በልጁ ደም እኔን ለገዛው (፪x)
ክብር ምስጋናዬ ይድረሰው
አዝማች · Chorus
ክበር ልለው አለሁ በፊቱ
ንገስ ልለው አለሁ በፊቱ
ግነን ልለው አለሁ በፊቱ (፪x)
ኃያል ክንደ ብርቱ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሥሙ ብርታቴ ሆኖኛል
ስዝል ደግፎ አቁሞኛል
በእርሱ ፀንቼ ቆሜያለሁ (፪x)
ጠላቴን እረግጫለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ