ክብሬ ነው
Kebrie New
ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሕይወቴ ክብር የሕይወቴ ቤዛ
የዘላለም ክብሬ ነው የሕይወቴ መዓዛ
ከእኔ ነው የምለው ምንም ሳይኖረኝ
እንዲሁ በፍቅር በፀጋው ዳንኩኝ(፪)
እስኪ ንገረኝ ምን ሰርቶልህ ነው
ምሕረት ፍቅር ፀጋ የምትለው
በዘመን ጊዜ በዓመታት ሁሉ
ያልተሰማ ነው የምትለው ሁሉ
አምላክ እንዲሁ ሰውን ወደደ
ለእኔ እና ለአንቺ ማለደ
ፍቅር ነው ፍቅር ነው
ከላይ ያስወረደው
አዝማች · Chorus
እኔ በራሴ ከምን ልበቃ
አድኖኝ እንጂ በፀጋ
ፍቅር ነው ፀጋ ነው
እኔን የሚያኖረኝ
ፍቅር ነው ኑሮዬ
ፍቅር ነው ደስታዬ
ፍቅር ነው የሚያኖረኝ
ፍቅር ነው ያከበረኝ
ፍቅር ነው ሕይወቴ
ፍቅር ነው ማጀቴ
ፍቅር ነው ኑሮዬ
ፍቅር ነው ዘላለሜ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሕይወት ምንጭ ነው የተጠጋው ያርፋል
የዘላለም ቤት ነው ከሲዖል ያድናል
እርሱ መዳኛ ነው የሞተው ሕይወት
እውነት ነው ኢየሱስ አይደለም ቅዠት
ክብሬ ነው ውበቴ
ጌጤ ነው ሽልማቴ
በእርሱ አረፍኩኝ ለዘላለም
ኢየሱሴ ነው የእኔ ዓለም
በእርሱ ብርሃን ሆነ ቤቴ
ጨለማ የለም በሕይወቴ
አዝማች · Chorus
ክብሬ ነው ውበቴ
ጌጤ ነው ሽልማቴ
በእርሱ አረፍኩኝ ለዘላለም
ኢየሱሴ ነው የእኔ ዓለም
በእርሱ ብርሃን ሆነ ቤቴ
ጨለማ የለም በሕይወቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ