ደራሽ
Derash
ትራክ 2 · አማርኛ
ደራሽ አለ ካህናችሁ
ከኢየሱስ ውጪ ማን አለ
ጠበቃ አለ ካህናችሁ
ከአባቴ ውጪ ማን አለ
አንድ እርምጃ ቀርቶ በእኔና በሞት
ጣልቃ ገብቶ አዳነኝ ድንገት በድንገት(፪)
አልተወኝም እንዲሁ እንዲሁ እንደዘበት
በድንገት ደረሰ ስሽቀዳደም ለሞት
አበቃለት ያለው የታለ ጠላቴ
ሞቴን ሲጠባበቅ ክብር ገባ ቤቴ
ለካ የመጨረሻውን አውቆ
የጠላቴ ድንፋታው አልቆ
በእጁ ድንገት ያስገባኝ ሲመስለው
ጌታ መጥቶ ታሪኬን ቀየረው
ክብር ይሁንለት ለክብሩ ዘላለም
እውነተኛ ዳኛ እንደ ጌታ የለም
የነፍሴ መዳኛ የክፉ ቀን ደራሼ
ስሙን ላወድሰው መልሼ መልሼ
"ትግርኛ" (ኤደን እምሩ)
?? ፍቅር ነው ኧረ ማን እንደርሱ
ፈጥኖ ሚያወጣ በድንገት ደርሶ
አዳኝ ደራሽ ማነው ካህናችሁ
በምሥጋናዬ ኑ ልንገራችሁ
እንኳን አበቃ ሲባል ኢየሱስ ነው
ደርሶ ከሞት የሚያድን ውድዬ ነው
ባማረ ዜማ ክብርን ልሰዋለት
ብዙ ውዳሴ ዕልልታ ይሁንለት
"ትግርኛ" (አቤኔዘር ታገሰ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ