Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኩራት ኩራት አለኝ

Kurat Kurat Alegn

7:18 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ብርቱ ተብሎ ታምኖበት ልብም በእርሱ ላይ ተጥሎ

አለልኝ ለእኔ እያለ መኖር ሲመኝ ተዘልሎ

የተደገፈው ሸንበቆ መሆኑን እንዲያው ሳያውቀው

ድንገት ተሰብሮ ወደቀ የዚያ ሰው መተማመኛው

አኔማ/እኔ ግን በላዬ ላይ ንጉሴን ሾሜያለሁ

አልፈራ አልደነግጥ በክንዱ እኮራለሁ (፪x)

ኩራት ኩራት አለኝ ብኮራስ ምናለ

እመካለሁ እኔስ ብመካ ምናለ

አንበሳው ኢየሱስ የእኔ ሆኖ የለ

ኃይለኛው ኢየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ

ኃይለኛው ኢየሱስ የእኔ ሆኖ የለ

ወዳጄ ኢየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ

እንዳንተ ያለ ከቶ የለምና

በሰማይ በምድር አልተገኘምና

ይብዛልህ ዛሬም ምሥጋና

ይብዛልህ ነገም ምሥጋና (፪x)

ዓይኔ አረፈብህ ወዳጄ በምንም የማትረታ

ወረት አታውቅም እንደሰው በጐ ነህ ሁሌ የእኔ ጌታ

ዘመናት ሲፈራረቁ አልተቀየረም መውደድህ

ሁሉን በጆችህ ይዘሃል ታስመካለህ ቢመኩብህ

በልቤ ሾሜሃለሁ ከፍ ብለህ ደምቀህ ታይ

እንዳንተ የለምና በምድር በሰማይ (፪x)

ኩራት ኩራት አለኝ ብኮራስ ምናለ

እመካለሁ እኔስ ብመካ ምናለ

አንበሳው ኢየሱስ የእኔ ሆኖ የለ

ኃይለኛው ኢየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ

ኃይለኛው ኢየሱስ የእኔ ሆኖ የለ

ወዳጄ ኢየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ

እንዳንተ ያለ ከቶ የለምና

በሰማይ በምድር አልተገኘምና

ይብዛልህ ዛሬም ምሥጋና

ይብዛልህ ነገም ምሥጋና (፪x)

በመከራ ቀን ቢጠሩት አለሁኝ የሚል ልብ ሞልቶ

ግራ ለገባው መጠጊያ ሚደግፍ እጁን ዘርግቶ

መተማመኛ ጌታ ነው ተፈትኖ አልፏል በብ

ደጋግ እጆቹን አይተናል ደካማዎቹን ሲያግዙ

አለልኝ ይሄ ጌታ የማይጥል የማይከዳ

ሰባራን የሚጠግን ወዳጅ ነው በምድረበዳ (፪x)

ኩራት ኩራት አለኝ ብኮራስ ምናለ

እመካለሁ እኔስ ብመካ ምናለ

አንበሳው ኢየሱስ የእኔ ሆኖ የለ

ኃይለኛው ኢየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ

ኃይለኛው ኢየሱስ የእኔ ሆኖ የለ

ወዳጄ ኢየሱስ ቤቴን ሞልቶት የለ

እንዳንተ ያለ ከቶ የለምና

በሰማይ በምድር አልተገኘምና

ይብዛልህ ዛሬም ምሥጋና

ይብዛልህ ነገም ምሥጋና (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ