ለበጐ ነው
Lebego New
2006 · ትራክ 1 · 5:53 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለበጐ ነው የሚሆነው ሁሉ
ተረድቼዋለሁ
የታለ አትበሉ ለእኔ ይታየኛል
ለእኔ ይታየኛል (፪x)
ያገኘኛል ያልኩት በእርግጥ ያገኘኛል
በእርግጥ ያገኘኛል (፪x)
የዘገየ ሲመስል በጊዘው ይመጣል
በጊዘው ይመጣል (፪x)
እንዳሳየኝ ያው እንዳለኝ ይሆናል
እንዳለኝ ይሆናል (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚሆነው ሁሉ ለበጐ ነው አውቃለሁ
አምላኬ በእኔ ላይ አላማው መልካም ነው (፪x)
(አላማው) አላማው መልካም ነው
(አላማው) አላማው መልካም ነው
(አላማው) አላማው ፍቅር ነው
(አላማው) አላማው የድል ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
የሌለውን ነገር እንዳለ አድርጐ ይጠራል
እንዳለ አድርጐ ይጠራል (፪x)
ለሙታን ሕይወትን ጌታዬ ይሰጣል
ጌታዬ ይሰጣል (፪x)
አበቃለት ሲባል ነገሩ ሲዘጋ
ነገሩ ሲዘጋ (፪x)
የሁሉ መክፈቻ ቁልፍ አለ እርሱ ጋር
ቁልፍ አለ እርሱ ጋር (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚሆነው ሁሉ ለበጐ ነው አውቃለሁ
አምላኬ በእኔ ላይ አላማው መልካም ነው (፪x)
(አላማው) አላማው መልካም ነው
(አላማው) አላማው መልካም ነው
(አላማው) አላማው ፍቅር ነው
(አላማው) አላማው የድል ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ማዕበሉ በዝቶ ወጀቡ ቢያይልም
ወጀቡ ቢያይልም (፪x)
ወደፊት ነው እንጂ ወደ ኋላ አልልም
ወደ ኋላ አልልም (፪x)
በውሃው ላይ ሆኖ ወደ እኔ ና ያለው
ወደ እኔ ና ያለው (፪x)
ሊያሰጥመኝ አይደለም እምነት ሊያሳየኝ ነው
እምነት ሊያሳየኝ ነው
ሊያሸጋግረኝ ነው
አዝማች · Chorus
የሚሆነው ሁሉ ለበጐ ነው አውቃለሁ
አምላኬ በእኔ ላይ አላማው መልካም ነው (፪x)
(አላማው) አላማው መልካም ነው
(አላማው) አላማው መልካም ነው
(አላማው) አላማው ፍቅር ነው
(አላማው) አላማው የድል ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
ከልካይ አይኑርብኝ ጌታን ላምልከው
አላማው በእኔ ላይ ሁሌም መልካም ነው
ሁሌም መልካም ነው
ጌታ መልካም ነው
ከሳሼ ገለል በል ጌታን ላክብረው
አላማው በእኔ እላይ ሁሌም መልካም ነው
ሁሌም መልካም ነው
ጌታ መልካም ነው
(አላማው) አላማው መልካም ነው
(አላማው) አላማው መልካም ነው
(አላማው) አላማው ፍቅር ነው
(አላማው) አላማው የድል ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ