ማምለክ ነው ስራዬ
Mamlek New Sraye
2016 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማምለክ ፤ ማምለክ :ነው ስራዬ፤
ሌላ ምን ልበልህ ጌታዬ፤
ሰማይና የብሱን ባህሩን ፈጥረሃል
አንተን ማምለክ ብቻ የኔ ስራ ሆንዋል
አዝማች · Chorus
ማድነቅ ፤ ማድነቅ ነው ስራዬ፤
ሌላ ምን ልበልህ ጌታዬ፤
ሰማይና የብሱን ባህሩን ፈጥረሃል
አንተን ማምለክ ብቻ የኔ ስራ ሆንዋል
ቁጥር 2 · Verse 2
ስራዬ ነው ጥሪዬ ነው፤
አንተን ማሞገስ ማወዳደሱ፤
ዕድል ፈንታዬ ዕጣ ክፍሌ፤
ኢየሱሴ ነው ለኔ ድርሻዬ
በጠዋትና በቀን በማታ፤
እንዳሞግስህ ክብርን እንዳመጣ፤
መሰዊያህንም እንዳሳምር፤
ለዚ ታላቅ ክብር እኔን ጠራህ
የሰማያት መለአክቱ፤
ያለማቋረጥ አንተን ያመልካሉ፤
ቅዱስ ቅዱስ እያሉ፤
ለተረደው በግ ስግደት ያመጣሉ
አዝማች · Chorus
እኔም እስግዳለው x3
እኔም አመልካለው
ሁሌም አመልካለው x2
ቁጥር 3 · Verse 3
እንዳመልክህ ከተፈጠርኩኝ፤
ደኃዋላ እንዴት እላለሁኝ፤
እንድሰዋ ከተሰራሁኝ፤
መሰዊያህን አሳምራለሁኝ
አምልኬ አምልኬ አምልኬ አልጠግብ አልኩኝ፤
ዘምሬ ዘምሬ ዘምሬ አልጠግብ አልኩኝ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ስላላገኘሁኝ
እንደ ኢየሱስ ያለ ስላላገኘሁኝ
አዝማች · Chorus
ማምለክ ማምለክ እግዚአብሔርን ማምለክ
እኔም ቤቴም ማምለክ
በጊዜውም ማምለክ
ያለጊዜው ማምለክ
ሲሆን ሳይሆን ማምለክ
ሲጨላልም ማምለክ
ሲነጋጋ ማምለክ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ