Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ንጉሥ ለወደደው

Negus Lewededew

2016 · ትራክ 1 · 4:54 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ንጉሥ ለወደደው እንዲህ ይደረግለታል

ንጉሥ ላፈቀረው እንዲህ ይደረግለታል

ንጉሥ ለወደደው ዘንጉ ይዘረጋለታል

ንጉሥ ላፈቀረው ካባ ይደረብለታል (፪x)

እኔን ስለወደደኝ ኢየሱስን ሰጠኝ

እኔን ስላፈቀረኝ መድኃኒትን ሰጠኝ

እኔን ስለወደደኝ አንድ ልጁን ሰጠኝ

እኔን ስላፈቀረኝ አማኑኤልን ሰጠኝ

ንጉሥ ስለወደደኝ እኔስ ዕድለኛ ነኝ

ንጉሥ ስላከበረኝ እኔስ ዕድለኛ ነኝ

ለእኔ የተደረገው ብዙ እኮ ነው

ለእኔ የተሰራው ብዙ እኮ ነው

አንድ በአንድ እቆጥራለሁ

የእርሱን መልካምነት እናገረዋለሁ (፪x)

ምን ያልተደረገ ያልሆነልኝ አለ

ከኢየሱስ ጀምሮ ለእኔ ያልተሰጠ

ከመልካምነቱ እኔን አጠገበ

ንጉሥ እኔን ወዶ እንዲህ አደረገ

ለእኔ የተደረገው ብዙ እኮ ነው

ለእኔ የተሰራው ብዙ እኮ ነው

አንድ በአንድ እቆጥራለሁ

የእርሱን መልካምነት እናገረዋለሁ (፪x)

አክሊል እንደለበሰ ያጌጠ ሙሽራ

ሕይወቴ በደሙ ታጥባ አምራ

በፊቱ የመግባትን ድፍረት አግኝታለች

ለልዑል እግዚአብሔር ዛሬ ታዜምለታለች

ቸር ነው (፪x)

ምሕረቱ ብዙ ነው

ፍቅሩ የማያልቅ ነው (፪x)

ወደደኝ አዳነኝ

ለክብሩ እኔን መረጠኝ (፪x)

(ወደደኝ አዳነኝ

ለክብሩ እኔን መረጠኝ (፪x))

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ