ማነው እንደ ኖህ
Manew Ende Noh
2014 · ትራክ 1 · 4:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዳዊት በዮናታን ዮናታን በዳዊት
ፍቅር ሲጀምር በነገስታት ቤት
በነፍስ ሲታሰር የፍቅር ኪዳን
አይለዋወጥ ፌዝ የለም ነበር
ሳኦል ሊገድለው ሲሻ ዳዊት
ያስመልጥ ነበር ቅን ዮናታን
የፍቅር ትርጉም ሲገባኝ እኔ
አንድ አላየሁም በዚህ ዘመኔ
ትናንት ሰው ሲሆን የወደድኩት
ዛሬ ኣውሬ ሆኖ ባይኔ አየሁት
ማታ በፍቅር የማለልኝ
ጠዋት ሰማሁት ሲዝትብኝ
ሲለዋወጥስ የጉራማይሌ
እጅጉን አዘንኩ ሲረሳ አምላኬ
አዝማች · Chorus
አዬ ክርስትናዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
ማነው እንደ ኖህ ኣለምን በጽድቁ የኮነነው
ኣንደበቱ ዝም ብሎ ህይወቱ የሚያወራው
በፍርድ ሚዛን ላይ ራሱን አስቀምጦ
ወንድሙን የሚያርድ በዝቶአል ከቃሉ አብልጦ
አታርገው ባዳ ኣታርገው ከንቱ
እቀፈው እንጂ እንደበፊቱ
ደም የፈሰሰው ቀራንዮ ላይ
ለዚህ እኮ ነው አንለያይ
አንለያይ!
ቁጥር 3 · Verse 3
ኧረ እስኪ ምን አልከን
ስንበላላ ስንነካከስ ስንጨራረስ ጌታችን
ምን ትለን ይሆን እስኪ ምን አልከን (፪x)
ቀንና ሌሊት መልካም አሳቢ
ለክፉ ነገር መልሱ ነው እምቢ
ዘመኑን ሙሉ ደግ እየኖረ
ፍቅር ሰባኪ ለእውነት ያደረ
ግን ይገርመኛል የዚህ ሰው ሕይወት
ምድር መከራ ጭንቅ የሆነችበት
ለእውነት ባደረ ምላሹ ሌላ
ምነው ይሄ ሰው ሚገፋው በዛ
አይሳመው እንጂ ልክ እንደ ይሁዳ
ያሴርበታል ሄዶ ከጓዳ
መንገዱ ቢመስል ውሎው ከጌታ
ልቡ ዴማስ ነው ሲገለጥ ማታ
አዝማች · Chorus
አዬ! ክርስትናዬ!
ቁጥር 4 · Verse 4
ዘመኑን ሙሉ ቤቱ አገልግሎ
በታማኝነት አምላኩን ብሎ
ደፋ ቀና ሲል ሰጥቶ ሕይወቱን
ድንገት ወደቀ ጥሎ ብርታቱን
በኃይሉ ጊዜ ያላነሱት
ዛሬ ሲወድቅ አስታወሱት
ከሰገባቸው ሰይፋቸው ወጣ
የትናንት ድካም ሁሉ እስኪረሳ
እንዳይመለስ እግዜሩን ፈርቶ
ወንድሙ ቆሞኣል ቢላውን ስሎ
ታዲያ ይሄ ሰው እንዴት ይመለስ
ፍርድ ካልመጣ ከሰማይ መቅደስ
አዝማች · Chorus
አዬ! ክርስትናዬ!!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ