Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መናህ ይጥመኛል

Menah Yetemegnal

ትራክ 4 · 3:37 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በአንተው እጅ ወድቄ ማልቀስ ይሻለኛል

ከፈርዖን ጮማ ለእኔ መናህ ይጥመኛል

፩ የሚቀጣ አባት ነው ጌታዬ ይህንን አውቃለሁ

በትርን በደስታ እቀበለዋለሁ

ያለመልመኛል አውቃለሁ

፪ የአንተን ጐጆ ጥዪ እልፍኙን ዛሬ ፊቴን ባዞር

ኋላ ለለቅሶ ነው በባዕድ ቤት ብኖር

ቅጣኝ አንተው ጌታ በአንተ እንድኖር

፫ ጥፋቴን መደበቅ አልችልም አምናለሁ በደሌን

በል እንካ ጀርባዬን ስጠኝ ግርፋቴን

በሚራራው እጅህ ቅጣቴን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ