ያለፈው በደሌን ተወው
Yalefewen Bedelien Tewew
ትራክ 2 · 3:20 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ያለፈው በደሌን ተወው
ጌታዬ አደራ አታስታውሰው
እባክህ እድል ስጠኝና
ልጅህ አድርገኝ እንደገና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በደሌ በዝቶ ባ'መጻዬ ታውሬያለሁ
እንደገና አውጣኝ በሃጥያቴ አለቅሳለሁ
የማልረባ ነኝ ኃይል የሌለኝ ብኩን ፍጡር
አንተን ሳይሆን ሟች ስጋዬን የማከብር
አዝማች · Chorus
ያለፈው በደሌን ተወው
ጌታዬ አደራ አታስታውሰው
እባክህ እድል ስጠኝና
ልጅህ አድርገኝ እንደገና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አዲስ ሰው አ'ርገኝ እንደ በረዶ የነጻ
ከታሰርኩበት ከስጋዬ አውጣኝ ነጻ
አትግፋኝ ጌታ በጥፋቴ አትመረር
ከተውከኝማ ወዴት አገር ሄጄ ልኖር
አዝማች · Chorus
ያለፈው በደሌን ተወው
ጌታዬ አደራ አታስታውሰው
እባክህ እድል ስጠኝና
ልጅህ አድርገኝ እንደገና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከእኔ የሚያስደስት አትጠብቅ አታገኝም
ስግብግብ ስጋ ተሸክሜ ከቶ አልነጻም
ብቻ ጌታዬ ፀጋህ ለ'ኔ ምሶሶዬ
ደጋፊዬ ነው እንዳትነሳኝ ባ'መፃዬ
አዝማች · Chorus
ያለፈው በደሌን ተወው
ጌታዬ አደራ አታስታውሰው
እባክህ እድል ስጠኝና
ልጅህ አድርገኝ እንደገና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ