እስካሁን ባጸናኝ
Eskahun Batsenagn
ትራክ 10 · 3:36 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
1. ሁሉን በሚያስችለው በጌታዬ ሆኜ
ወደ ፊት አያለሁ በእርሱ ላይ ታምኜ
የሰይጣን እቅፋት ፈተናው ቢረቅቅም
በጌታዬ እስካለሁ አልነቃነቅም
አዝማች · Chorus
እስካሁን ባፀናኝ አሁንም እፀናለሁ (፪×)
ኃይሉ የኢየሱስ ነው ለምን እፈራለሁ (፪×)
ቁጥር 2 · Verse 2
2. ዕለት ዕለት ቀርፆኝ እያስተካከለኝ
ፈቃዱ ነው ጌታ መንገዴን ሊመራኝ
ከዓይኑ አይለየኝም መንገዴን እንዳልስት
እረኛዬ አምላኬ እኔም የእርሱ ጠቦት
አዝማች · Chorus
እስካሁን ባፀናኝ አሁንም እፀናለሁ (፪×)
ኃይሉ የኢየሱስ ነው ለምን እፈራለሁ (፪×)
ቁጥር 3 · Verse 3
3. ለድካሜ ብርታት ከጌታ እያገኘሁ
በፀጋው እንዳለሁ አሁንም እኖራለሁ
እየተማፀንኩኝ አምላኬ እንዳይተወኝ
ከጽዮን እንድደርስ በጌታ እምነት አለኝ
አዝማች · Chorus
እስካሁን ባፀናኝ አሁንም እፀናለሁ (፪×)
ኃይሉ የኢየሱስ ነው ለምን እፈራለሁ (፪×)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ