መሪዬ ነህ
Meriyie Neh
2016 · ትራክ 1 · አማርኛ
በምድረበዳው(፪)
ጥሎ የማይሄድ ጌታ የሚያሳርፍ ነው
ከእናቴ ማህጸን ስላወቀኝ ጌታ
እንዳልጠፋ እንዳልሞት በብዙ ጥበቃ
እየጠበቀኝ እየደገፈኝ
እረኛዬ ሆኖ ጌታ አሳደገኝ
መሪዬ ነህ ለእኔ ብልህ ምን ያንስሃል ኢየሱሴ
ውበት ደምግባቴ ብልህ ምን ያንስሃል ኢየሱሴ(፪)
በመከራዬ ላይ ጋሻ የሆነኝ
ተስፋ በሌለበት ፍቅሩ እኮ ነው እጄን የያዘኝ
ከማንም አብልጦ እኔን ሚጠጋጋ
(ኢየሱስ እኮ ነው የእኔ ዋስ ጠበቃ)፪
የገረመኝ(፫) የጌታ ማዳን ለእኔ ገብቶኝ
የደነቀኝ(፪) የጌታ ፍቅር ለእኔ ገብቶኝ
እናገራለሁ አፌን ሞልቼ
??? በሮቼን
በምሥጋና(፫) ስሙን ላክብር እንደገና
በዕልልታ(፫) ዛሬም አለሁ በከፍታ
ክብሩን ትቶ ለእኔ ከሰማይ መጣልኝ
እዳዬን ከፈለ ከሲዖል አወጣኝ
ምን ልበል እንግዲህ ቃላቶች የሉኝም
የፍቅሩን ጥልቀት መግለጽ አልቻልኩኝም
የገረመኝ(፫) የጌታ ማዳን ለእኔ ገብቶኝ
የደነቀኝ(፪) የጌታ ፍቅር ለእኔ ገብቶኝ
እናገራለሁ አፌን ሞልቼ
??? በሮቼን
በምሥጋና(፫) ስሙን ላክብር እንደገና
በዕልልታ(፫) ዛሬም አለሁ በከፍታ
ማቄ ተቀደደ ዳግም ተወለድኩኝ
ልጅ የምሆንለት አባት አገኘሁኝ
ይኸው በተራዬ እመሰክራለሁ
ኢየሱስ ያድናል ብዬ አወራለሁ
የገረመኝ(፫) የጌታ ማዳን ለእኔ ገብቶኝ
የደነቀኝ(፪) የጌታ ፍቅር ለእኔ ገብቶኝ
እናገራለሁ አፌን ሞልቼ
??? በሮቼን
በምሥጋና(፫) ስሙን ላክብር እንደገና
በዕልልታ(፫) ዛሬም አለሁ በከፍታ
በምድረበዳው(፪)
ጥሎ የማይሄድ ጌታ የሚያሳርፍ ነው
ከእናቴ ማህጸን ስላወቀኝ ጌታ
እንዳልጠፋ እንዳልሞት በብዙ ጥበቃ
እየጠበቀኝ እየደገፈኝ
እረኛዬ ሆኖ ጌታ አሳደገኝ
መሪዬ ነህ ለእኔ ብልህ ምን ያንስሃል ኢየሱሴ
ውበት ደምግባቴ ብልህ ምን ያንስሃል ኢየሱሴ(፪)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ